ብራዚላዊው ኮከብ ማርሴሎ ከተጫዋችነት ራሱን አገለለ

ብራዚላዊው ኮከብ ማርሴሎ ከተጫዋችነት ራሱን አገለለ

ብራዚላዊው ኮከብ ማርሴሎ ቬራ ዳ ሲልቫ ጁኒዬር ከእግርኳስ ተጫዋችነት ራሱን በይፋ አግልሏል።

የቀድሞ የሪያል ማድሪድ ተጫዋች በ36 ዓመቱ ነው ጫማ መስቀሉን ያሳወቀው።

የግራ መስመሩ ተከላካይ ዳግም ከተቀላቀለው  ከልጅነት ክለቡ ፍሉሚኔንስ ጋር ከተለያየ በኋላ ያለፉትን  ሶስት ወራት ያለክለብ ቆይቷል።

ለ15 ዓመታትን በሪያል ማድሪድ ተጫውቶ ያሳለፈው ማርሴሎ ከሎስብላንኮቹ ጋር 6 የላሊጋ እና 5 የአውሮፓ ቻምፒየንስሊግ ዋንጫን ጨምሮ 25 ትልልቅ ዋንጫዎችን አሳክቷል።

የማጥቃት ባህሪ ያለው የመስመር ተከላካይ በነጩ ማልያ 714 ጨዋታዎችን አከናውኖ 58 ጎሎችን ከመረብ አሳርፏል።

በሪያል ማድሪድ እግርኳስ ክለብ 117 ዓመታት ታሪክ ከስፔናዊ ተጫዋች ውጪ ሆኖ ክለቡን በአምበልነት በመምራት ፈር ቀዳጅ መሆን የቻለው ማርሴሎ ለብራዚል ብሔራዊ ቡድን 58 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፏል።

እንደ አውሮፓውያኑ በ2022 ከስፔኑ ክለብ ጋር በመለያየቱ ወደ ግሪክ አቅንቶ ለኦሎምፒያኮስ ለአምስት ወራት መጫወቱ ይታወሳል።

በሙሉቀን ባሳ