ጇኦ ፌሊክስ ወደ ኤሲ ሚላን ለመዛወር ተስማማ

ጇኦ ፌሊክስ ወደ ኤሲ ሚላን ለመዛወር ተስማማ

የቼልሲው የፊት መስመር ተጫዋች ጇኦ ፌሊክስ በውሰት ወደ ጣሊያኑ ክለብ ኤሲሚላን ለመዛወር መስማማቱ ተዘግቧል።

ኤሲ ሚላን ተጫዋቹን በቋሚነት የማዛወር ስምምነት ያልተካተተ ሲሆን ለውሰት ውሉ ግን 5 ሚሊዮን ፓውንድ ይከፍላል ተብሏል።

የእንግሊዙ ክለብ ማንቸስተር ሲቲ ሊዘጋ ሰዓታት በቀሩት የጥር የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት የአማካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነውን ኒኮ ጎንዛሌዝን ከ ፖርቶ ለማስፈረም መስማማቱ ተገልጿል።

የ23 ዓመቱ ስፔናዊው ተጫዋች በዘንድሮው የጥር የተጫዋቾች ዝውውር አራተኛው ፈራሚ ይሆናል።

በሌላ በኩል በማንቸስተር ዩናይትድ እና አርሰናል በጥብቅ ይፈለግ የነበረው ማቲያስ ቴል ከባየርን ሙኒክ በውሰት ቶትንሃምን ለመቀላቀል መስማማቱ ተነግሯል።

ዌስትሃም ዩናይትድ በበኩሉ ኢቨን ፈርጉሰንን ከብራይተን በውሰት ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።

ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ