የአካባቢን ሰላም ለማስጠበቅ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ትልቅ ሐላፊነት መዉሰድ እንዳለባቸዉ ተጠቆመ
በደቡብ ኦሞ ዞን ኛንጋቶም ወረዳ የካንጋቲን ከተማ ያለዉን ሠላም ለማስቀጠልና በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ባለቤቶች እንዲሁም ከከተማዋ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር በሰላም ዙሪያ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
ከተሳታፊዎቹ ስለ ሠላም የማህበረሰብ ዉይይቶች ማካሄድ ጠቃሚ በመሆናቸዉ ተጠናክረው እንዲቀጥል ጠቁመዉ ለጋራ ሰላም የበኩላቸዉን ሚና እንደሚወጡ ተናግረዋል።
መድረኩን የመሩት የወረዳዉ ፖሊስ ጽ/ቤት የስታፍ ስራ ማስተባበሪያ ሐላፊ ኢንስፔክተር በድሉ ማሞ እና የወንጀል መከላከል ሐላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ሎፔቶ ሎቡን እንደገለጹት፤ የዉይይቱ ዓላማ የከተማዋን ሠላም ለማስቀጠል ማህበረሰቡ ከፖሊስ ጎን እንዲቆሙ ለማስቻል መሆኑን ጠቅሰዉ የአካባቢዉንና የከተማዋን ሠላም ለማስጠበቅ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ባለቤቶች ሐላፊነት እንዳለባቸዉ አመላክተዋል።
አያይዘዉም ከህብረተሠቡ እየተነሱ የነበሩት ገንቢ አስተያየቶችን ወስዶ የወረዳዉ ፖሊስ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ለወንጀል መንስኤ ናቸዉ በሚባሉ ጉዳዮች ላይ ልዩ ክትትል በማድረግ እንደሚሠራ አብራርተዋል።
ዘጋቢ፡ ወንድማገኝ በቀለ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
በሁሉም ዘርፍ ለሚከናወኑ ስራዎች የመንገድ መሰረት ልማት ጠቀሜታው ፈርጀ ብዙ መሆኑ ተገለፀ
የቀን 6፡00 ዜና 24፤ ሀዋሳ፡ ጥር 13/2017 ዓ.ም
በህብረ ብሔራዊ አንድነት የብልጽግና ፓርቲ ጉዞ እውን እንዲሆን የፓርቲው አባላት ግንባር ቀደም ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተገለፀ