የጉራጌ ዞን አስተዳደር 75 ሺህ 9 መቶ 60 ሄክታር መሬት ላይ የስነ-አካላዊ ስራ ለማከናወን ወደ ተግባር መግባቱን ገለፀ
በዞኑ የ2017 ዓ.ም ዞናዊ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ በእንደጋኝ ወረዳ በይፋ ተጀምሯል።
የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ “የተቀናጀ ግብርና ለቤተሰብ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል ዞናዊ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት፤ የተፋሰስ ልማት በዞኑ ባህል እየሆነ በየአመቱ በርካታ ለውጦች እያመጣ ሲሆን የአፈርና ውሃ በመጠበቅ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በክልል እና በፌደራል ሞዴል የሆኑ ስራዎች ተሰርተዋል።
በመሆኑም በዘንድሮው ዓመትም በትኩረት እንደሚሰራበት አስታውቀዋል።
በዞኑ በተፋሰስ ልማት ከ3 መቶ 90 ሺህ በላይ ህዝብ በማሳተፍ 75 ሺህ 9 መቶ 60 ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል ምክትል አስተዳዳሪው።
የተፋሰስ ልማት እንዱ አላማ ያልታረሱ መሬቶች እንዲታረሱ ማድረግ፣ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል፣ የተጎዱ መሬቶች ማከም፣ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ መስራትና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ማድረግ እንደሆነ ነው የተናገሩት።
የሰው ሀይል አቅም በአግባቡ በመጠቀም የተፉሰስ ስራ ከዚህ ቀደም ከነበረው በጥራት፣ በፍጥነትና ምርታማነትን በሚያመጣ መልኩ መስራት እንደሚገባ አቶ አበራ አስገንዝበዋል።
አርሶ አደሩ የተፋሰስ ልማት ስራ ሲሰራ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያ፣ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ እራሱን የሚቀየርበት ወቅት ነው ያሉት አቶ አበራ፤ ስራው ሲሰራ የአርሶ አደሩን እና የወጣቱ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል።
የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊና የተፈጥሮ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አድማሱ ፍቅሬ በበኩላቸው፤ በዞኑ የሚገኙ 271 ተፋሰሶች ለማልማት ታቀዶ ወደ ተግባር ተገብቷል ብለዋል።
ባለፋት አመታት በተፋሰስ ልማት አማካኝነት ምርት የማይሰጡ ቦታዎች ለምተው በግጦሽና በተለያዩ ሰብሎች በመሸፈን አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን በመግለፅ ተግባሩ በጥራትና በስፋት ለማከናወን በዞኑ በሁሉም መዋቅሮች ተግባራዊ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን ተናግረዋል።
የእንደገኝ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሉቀን ገዙ በበኩላቸው፤ የወረዳው አርሶ አደር ከዚህ ቀደም በተሰሩ የስነ-አካላዊ እና ስነ-ህይወታዊ ስራዎች ተጠቃሚ በመሆኑ ተግባሩ ባህል አድርጎት እያከናወነው እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
አክለውም ተግባሩ በወረዳው በ17ቱም ቀበሌዎች 4ሺህ 783 ሄክታር መሬት በ2007 ዓ.ም የተፋሰስ ንቅናቄ እንደሚለማ አቶ ሙሉቀን ጠቁመው ለዚህ ተግባር 23ሺህ የሰው ኃይል እንዲሁም 26ሺህ ቁሳቁስ ተለይቶ ወደ ተግባር ተገብተዋል ብለዋል።
አርሶ አደሩ በስነ-አካላዊም ሆነ ስነ-ህይወታዊ ስራ የሰራባቸው ቦታዎች ከሰውንና ከእንስሳት ንክኪ በመጠበቅ እንዲሁም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ባላቸው ዛፎችና ሰብሎች በመሸፈን ዘላቂ ምርትና ምርትና ምርታማነትን ማረጋገጥ እንደሚጠበቅበት አስረድተዋል፡፡
አቶ አብራር ክብሮ እና ወ/ሮ ፈለቀች ደገፋ በእንደጋኝ ወረዳ ገነት ቀበሌ የተፋሰስ ልማት ስራ ሲሰሩ ያገኘናቸው አርሶ አደሮች ሲሆኑ የተፋሰስ ልማት መስራት ማለት አፈርን እንደማከም ነው ብለዋል።
መሬት እንዳይሸረሸር፣ የመሬት ናዳ እንዳይከሰት፣ የውሃ እጥረት እንዳይገጥም በርካታ ጥቅም ያለው ሲሆን በቦታው ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያላቸው ችግኞች በመትከል የወተት ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ያደርጋል ነው ያሉት።
በየአመቱ የተፋሰስ ስራ በጉጉት ጠብቀን በሰራናቸው ስራዎች ምርትና ምርታማነታችን እንዲጨምር አስችሏል ያሉት አርሶ አደሮቹ በቀጣይም አጠናክረን እንሰራለን ብለዋል።
ዘጋቢ፡ ሪድዋን ሰፋ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ቋሚ ኮሚቴ የሚከታተላቸውን ተቋማት የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀመረ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከ12 ቢሊየን ብር በላይ በጀት 471 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ እየተሰራ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ
የ2017 ዓ.ም የተቀናጀ የተፋሠሰ ልማት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በየም ዞን ፎፋ ወረዳ በአዝጊ ዘምዳ ቀበሌ ተጀመረ