አስቶንቪላ ማርከስ ራሽፎርድን እና ማርኮ አሴንሲዮን ሊያስፈርም ነው
የእንግሊዙ ክለብ አስቶንቪላ ማርከስ ራሽፎርድን ከማንቸስተር ዩናይትድ እንዲሁም ማርኮ አሴንሲዮን ከፒኤስጂ በውሰት ለማስፈረም ከስምምነት ላይ መድረሱ ተነግሯል።
ከህዳር ወር አንስቶ በሩበን አሞሪም በሚመራው የቀያይ ሰይጣኖች ዋናው ቡድን ስብስብ ውስጥ መካተት ያልቻለው ማርከስ ራሽፎርድ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ወደ አስቶንቪላ እንደሚያቀናም ተነግሯል።
በማንቸስተር ዩናይትድ እስከ 2028 ድረስ የሚያቆየው ኮንትራት ላለው ማርከስ ራሽፎርድ በውሰት ቆይታውም አስቶንቪላ 70 በመቶ የሚሆነውን ሳምንታዊ የደመወዝ ክፍያ ይከፍላል ተብሏል።
የካሪንግተን አካዳሚ ፍሬ የሆነው ማርከስ ራሽፎርድ በትያትር ኦፍ ድሪምስ እስካሁን ለዋናው ቡድን ከ400 በላይ ጨዋታዎችን አከናውኖ 138 ጎሎችን ከመረብ አሳርፏል።
በተጨማሪም በአሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የሚመራው አስቶንቪላ እስፔናዊውን የፊት መስመር ተጫዋች ማርኮ አሴንሲዮን ከፒኤስጂ እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በሚቆይ የውሰት ውል ለማስፈረም ተስማምቷል።
አስቶንቪላ ለቀድሞው የሪያል ማድሪድ ተጫዋች በፒኤስጂ የሚከፈለውን ሳምንታዊ የደመወዝ ክፍያ ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል ተብሏል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ሪያል ማድሪድ ማንቸስተር ሲቲን በደርሶ መልስ አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ
ሊቨርፑል ዎልቭስን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ
አትሌት ዩሚፍ ቀጀልቻ በ10 ኪሎ ሜትር የግሉን እና የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈ