የጥንቃቄ መልዕክት-ዶክተር ደግነት አማዶ (የድንገተኛ እና ጽኑ ህሙማን ስፔሻሊስት )
በዶ/ር ቦጋለች መታሰቢያ አጠቃላይ ሆስፒታል” የድንገተኛ እና ጽኑ ህሙማን ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ደግነት አማዶ ቅባትና ስብ የበዛባቸው ምግቦችን ማብዛት ጉዳቱ የከፋ ነው ይላሉ ፡፡
ከቅባት ምግቦች በተጨማሪ አትክልቶችና ፍራፍሬዎን በስብጥር መመገብ እንደሚገባም በማለት ይመክራሉ ።
በጾም ወራት ለተወሰነ ጊዜ ከፍስግ ምግቦች እርቀው የቆዩ ግለሰቦች ቶሎ ለቅባታማ ምግቦች በሚጋለጡበት ጊዜ ለተለያዩ ተላላፊ ላልሆኑ የጤና እክሎች ሊገጥሟቸው እንደሚችል የሚናገሩት ዶ/ር ደግነት ቅባትና ስብ የበዘባቸውን ምግቦች ማዘውተር ለደም ግፊት፣ ለልብ ህመም ፣ለኮሌስትሮል መጨመር ለጨጓራ ህመምና ለመሳሰሉት በሽታዎች ሊያጋልጥ እንደሚችል ዶክተር ደግነት አብራርተዋል ።
የሀገራችን የስብጥር አመጋገብ ባህል አነስተኛ ነው ያሉት ዶ/ር ደግነት የአትክልትና ፍራፍሬ ገበታን በማብዛት ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና እክሎችን መከላከል እንደሚገባም አሳስበዋል ።
ዘጋቢ : መልካሙ ታፈሠ -ከሆሳዕና ጣቢያችን።

More Stories
የጡት ካንሰር ተገቢው ህክምና በወቅቱ ካልተደረገ ለከፋ አደጋ የሚያጋልጥ እንደመሆኑ ድንገት ሲያጋጥም በባህል ህክምና ከመዘናጋት ይልቅ በአፋጠኝ ወደ ጤና ተቋማት መሄድ ተገቢ ነው – ዶክተር ተሾመ አለምቦ
ህብረተሰቡ በሽታን ለመከላከል የሚሰጡ ክትባቶችን በአግባቡ በመውሰድ እንዳለበት ተገለጸ
የመስቀል በዓል አከባበር ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ካስመዘገበቻቸው የማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል አንዱ ነው