አትሌት ደዊት ወልዴ እና ሩቲ አጋ በዢያሜን ማራቶን የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፉ
በቻይና ዢያሜን በተካሄደ የ2025 የማራቶን ውድድር አትሌት ዳዊት ወልዴ እና ሩቲ አጋ የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፈዋል።
በወንዶች ማራቶን አትሌት ዳዊት ወልዴ 2 ሰዓት ከ06 ደቂቃ ከ06 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት የቦታውን ክብረወሰን በመስበር ማሸነፍ ችሏል።
በውድድሩ ሌላኛው ኢትዮጵያዊው አትሌት አሰፋ ቦኪ በ26 ሴኮንዶች ተቀድሞ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።
በሴቶች ማራቶን ደግሞ አትሌት ሩቲ አጋ 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ46 ሴኮንድ በተመሳሳይ የቦታውን ክብረወሰን በመስበር አሸንፋለች።
እንዲሁም አትሌት ጉተሚ ሾኔ 2 ሰዓት ከ23 ደቂቃ ከ11 ሴኮንድ 2ኛ፣አትሌት ፍቅርተ ወረታ 2፡23፡15 ሴኮንድ 3ኛ በመውጣት ተከታትለው በመግባት ማሸነፍ ችለዋል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ
More Stories
በላንክሻየር ደርቢ ሊቨርፑል ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ዛሬ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አርሰናል ከቦክሲንግ ዴይ ማግስት ምሽት ላይ ኢፕሲች ታውንን ያስተናግዳል
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቤቶች አካል ብቃት እንቅስቃሴ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሄደ