አርሰናል ከቦክሲንግ ዴይ ማግስት ምሽት ላይ ኢፕሲች ታውንን ያስተናግዳል
በ18ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬርሊግ መርሐግብር አርሰናል ከቦክሲንግ ዴይ ማግስት በሜዳው ኢፕሲች ታውንን ምሽት 5 ሰዓት ከ15 ላይ ያስተናግዳል።
ሁለቱ ክለቦች በፕሪሚዬርሊጉ ከ22 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚገናኙበት ጨዋታ አርሰናል ጨዋታውን በማሸነፍ ይበልጥ ወደ ዋንጫ ፉክክሩ ለመቅረብ እንዲሁም አዲስ አዳጊው ክለብ ከወራጅ ቀጠናው ለመውጣት ይጫወታል።
በኤምሬት ስታዲዬም በፕሪሚዬርሊጉ ባለፉት 11 ጨዋታዎች ባለመሸነፍ እየተጓዘ የሚገኘው አርሰናል የምሽቱን ጨዋታ ማሸነፍ የሚችል ከሆነ 2ኛ ደረጃን ይይዛል።
ኢፕሲች ታውን በበኩሉ ከወራጅ ቀጠናው ለመራቅ ከሚያደርጉት ፊልሚያ በተጨማሪ የሰሜን ለንደኑን ክለብ እንደ አውሮፓዊያኑ ከ1984 ወዲህ ወይም ከ13 ጨዋታዎች በኋላ የመጀመሪያ ድሉን ለማሳካት ወደሜዳ ይገባል ተብሎ ይታሰባል።
በአርሰናል በኩል ቡካዮ ሳካ፣ ስተርሊንግ፣ ቤን ኋት በጉዳት ምክንያት በጨዋታው እንደማይሰለፉ ሲገለፅ፤ ዚንቼንኮ ግን ከጉዳት አገግሞ ለምሽቱ ጨዋታ ብቁ ነው ተብሏል።
ከዚህ ጨዋታ ቀደም ብሎ በአሜክስ ስታዲየም ብራይተን ከብሬንትፎርድ ይጫወታሉ።
ያለፉትን ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻለው ብራይተን ወደ ድል ለመመለስ እንዲሁም ከሜዳው ውጪ ደካማ ውጤት ማስመዝገብ የቻለው ብሬንትፎርድ በውድድር ዓመቱ ከሜዳው ውጪ ለመጀመሪያ ጊዜ ለማሸነፍ ይጫወታሉ።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ሀገር አቀፍ የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ያለምንም ችግር እንዲካሄድ በቂ ዝግጅት መደረጉን የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ ገለፁ
ዳራማሎ ደንዳሾ ስፖርት ክለብ ባስኬት ቡናን በማሸነፍ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የዋንጫ አሸናፊ ሆነ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ለፍፃሜ ያለፉ ክለቦች ተለይተው ታውቀዋል