የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከቻን ውድድር ውጪ ሆነ
ሀዋሳ፡ ታህሳስ 16/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ2024 የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ(ቻን) በሁለተኛ ዙር ማጣሪያ በሱዳን በድምር ውጤት ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ሆኗል።
ዛሬ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ በሊቢያ ቤንጋዚ በቤኒና ማርትርየስ ስታዲየም የመልስ ጨዋታውን ያከናወነው ብሔራዊ 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።
ለሱዳን የማሸነፊያ ግቦችን ሞሲ ኮናቴ በ16ኛው ደቂቃ እና መሐመድ አብዱራህማን በ69ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ደግሞ ብቸኛዋን ግብ ብርሀኑ በቀለ በ63ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎ ዋልያዉ በድምር ውጤት 4ለ1 ተሸንፎ ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።
ዘጋቢ፡ በሙሉቀን ባሳ
More Stories
2ኛው የየም ዞን ስፖርት ሻምፕዮና በሣጃ ከተማ እየተካሄደ ነው
የ2017 የጋሞ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና ውድድር በወንዶች እግር ኳስ ውድድር በዳራማሎ ወረዳ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ