የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ከቶትንሃም ጋር ዛሬ የሚያከናውኑት ጨዋታ ይጠበቃል
በእንግሊዝ ፕሪሚዬርሊግ 17ኛ ሳምንት መርሐግብር የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ከቶትንሃም በቶትንሃም ስታዲዮም ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ የሚያከናውኑት ጨዋታ ይጠበቃል።
በሁሉም ውድድሮች ካከናወናቸው ያለፉት 24 ጨዋታዎች መካከል 20ቹን በማሸነፍ በአንዱ ብቻ ሽንፈትን ያስተናገደው ሊቨርፑል ከአራት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈረንጆችን ገና የሊጉ መሪ ሆኖ ለመቀበል ይጫወታል።
የመርሲሳይዱ ክለብ ከቶትንሃም ጋር ካከናወናቸው ያለፉት 23 ጨዋታዎች የተሸነፈው በአንድ ጨዋታ ብቻ ነው። በ16 ግጥሚያዎች ማሸነፍ ሲችል በ6 ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል።
በቶትንሃም በኩል ግብ ጠባቂውን ጉግሊኤልሞ ቪካሪዎ፣ክርስቲያን ሮሜሮ እና ሪቻርልሰንን ጨምሮ 8 ተጫዋቾች በጉዳት ምክንያት አይሰለፉም ተብሏል።ዴስቲኒ ኡዶጊ ግን ለጨዋታው እንደሚደርስ ተገልጿል።
በሊቨርፑል በኩል አንዲ ሮበርትሰን ከቅጣት የሚመለስ ሲሆን ኮነር ብራድሌይ እና ኢብራሂማ ኮናቴ በጉዳት በዛሬው ጨዋታ አይሰለፉም።
ከዚህ ጨዋታ ቀደም ብሎ 4 ጨዋታዎች በተመሳሳይ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ ይካሄዳሉ።
በዚህም መሰረት ኤቨርተን ከቼልሲ፣ማንቸስተር ዩናይትድ ከበርንማውዝ፣ሌስተር ሲቲ ከዎልቭስ እንዲሁም ፉልሃም ከሳውዝሃምተን የሚጫወቱ ይሆናል።
በሙሉቀን ባሳ
More Stories
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጠው
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች