ሀዋሳ፡ የካቲት 04/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ”ሃይማኖቶች ለሰላም ለመከባበር እና ለአንድነት” በሚል መሪ ቃል ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሆሳዕና ከተማ የሚካሄደው የሰላም ኮንፍራንስ ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛል።
በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር እና የዕለቱ የክብር እንግዳ እንደሻው ጣሰው(ዶ/ር)፣ ብፁዕ አቡና ህርያቆስ የአዲስ አበባና ሀድያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ፓትርያርኩና የኢሃተጉ የበላይ ጠባቂ ተወካይ፣ ክቡር ሽይኽ አብዱልከሪም ሽይኽ በድረዲን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንትና የፕሬዝዳንቱና የኢሃተጉ የበላይ ጠባቂ ተወካይ፣ ክቡር ቄስ ደረጄ ጀምበሩ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ከውንስል ፕሬዚዳንትና የኢሃተጉ የበላይ ጠባቂ ተወካይ፣ ብፁዕ አቡነ ስዩም ፍራንሷ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የብፁህ ካርዲናልና የኢሃተጉ የበላይ ጠባቂ ተወካይ፣ ፓስተር ታደሠ አዱኛ የኢትዮጵያ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንትና የኢሃተጉ የበላይ ጠባቂ ተወካይ እንዲሁም የሃይማኖት መሪዎች የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀድያ ዞን እና የሆሣዕና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ በየነ ሰላሙ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
መደበኛ ባልሆነ መልኩ የሎተሪ ዕድል ሙከራን “ዕቁብ” በሚል ሽፋን በህገ-ወጥ ተግባር ላይ የተሳተፉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት አሳሰበ
መንግስት ባለፉት ጊዜያት በስርዓተ ትምህርት እና በመማር ማስተማር ሂደት የነበረውን ክፍተት ለመሙላት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በጥናትና ምርምር የተደገፈ ስራ በመስራት መደገፍ እንደአለባቸው ተገለጸ
የአብሮነት ምልዕክት