በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 6ኛው ሀገር አቀፍ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ እየተካሔደ ነው።
በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሳቢሳቢ ብፅዕ አቡነ መልከፀዴቅ ሲምፖዜሙ አብሮነትን ለማጠናከር የጋራ ሰላምን ለማጽናት ትኩረት ያደረገ እንደሆነ ጠቁመዋል።
የቋንቋና የእምነት ብዝሃነት ቢኖርም ብዝሃነት ውበት መሆኑን በመገንዘብ ከልዩነት በላይ እጅግ በርካታ አንድ የሚያደርጉ የጋራ ጉዳዮች ስላሉ ልዩነትን አክብረን በጋራ አጀንዳዎቻችን ላይ ለጋራ ጥቅም መወያየት እና መስራት ይገባል ብለዋል።
ሀይማኖት የግጭት ምንጭ መሆን አይገባም ያሉት አቡኑ መልከፀዴቅ በሁሉም ቤተ እምነቶች ፈጠሪ ያዘዘውን ሰላምን፣ መተባበርን፣ መረዳዳትንና አንድነት አጥብቀን መያዝ እንደሚገባም መክረዋል።
መለያየት የውድቀት ምልክት ነው ያሉት አቡኑ፥ አንድነትን ለማጠናከር በጋራ መስረት እንደሚገባም አመልክተዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር፣ እና የዕለቱ የክብር እንግዳ እንደሻው ጣሰዉ (ዶ/ር) ባለፉት ስድስት ዓመታት በፖለቲካዊ በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የላቀ ውጤት መመዝገቡን አብራርተዋል።
በሀገሪቱ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች መፈታታቸውን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ መንግስት በከፍተኛ የስራ ኃላፊነት ተሳትፎ እንዲኖራቸው መደረጉን አብራርተዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ለዜጎች ሁለንተናዊ እድገት ተጠቃሚነት በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ዶክተር እንዳሻ ገልጸዋል።
በሀገራችን ስር የሰደዱ ችግሮችንና ግጭቶችን ለመፍታት ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።
በምክክር ኮሚሽኑ በሁሉም አካባቢዎች ህዝቡ የሚያነሳቸው የጋራ ጥያቄዎች እየተሰበሰቡ የጋራ መፍትሄ ለመምጣት ጠቃሚ መሆኑንም አክለዋል።
በማህበራዊ ዘርፍ በትምህርትና ጤና ዘርፍ አበረታች ውጤት ለማምጣት ጥረት እየተደረገ እንደሆነም አንስተዋል።
ሁሉንም ነገር ለማከናወን ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ያጋጠሙ ችግሮች እና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በጋራ ጥረት ተደርገዋል ብለዋል።
ክልሉ ከተመሰረተ ወዲህ የሰላምን ስራ ቀዳሚ አጀንዳ በማድረግ እየተሰራ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህ ጉባኤ የክልሉን ሰላም በማጽናት ረገድ ጉልህ ሚና እንዳለውም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።
ዘጋቢ: በየነ ሰላሙ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
ከመማር ማስተማር ተግባር ባለፈ የአካባቢ ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን የሚዛን ግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ አስታወቀ
የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ(ዶ/ር) መጭው ጊዜ ከተስፋ ብርሃን ወደሚጨበጥ ብርሃን የምንሸጋገርበት ብሩህ ዘመን መሆኑን ተናገሩ
በተቀሩት አጭር ቀናት ህብረተሠቡ የመራጭነት ካርዱን በመውሰድ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳና አካባቢው የፌደራልና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጥሪ አቀረቡ