ማንቸስተር ሲቲ በአስቶንቪላ ተሸነፈ
በ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬርሊግ ማንቸስተር ሲቲ በአስቶንቪላ 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።
የአስቶንቪላን የማሸነፊያ ግቦች ጆን ዱራን እና ሞርጋን ሮጀርስ ከመረብ አሳርፈዋል።
ማንቸስተር ሲቲን ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ ፊል ፎደን አስቆጥሯል።
ማንቸስተር ሲቲ እንደ አውሮፓውያኑ ከ2001 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሜዳው ውጪ በ8 ተከታታይ ጨዋታዎች ሁለት እና ከዛ በላይ ተቆጥረውበታል።
ፕሪሚዬር ሊጉ መካሄዱን ሲቀጥል በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ብሬንትፎርድ ከኖቲንግሃም ፎረስት፣ ኢፕሲች ታውን ከኒውካስል ዩናይትድ እንዲሁም ዌስትሃም ዩናይትድ ከብራይተን ይጫወታሉ።
ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ላይ ደግሞ በለንደን ደርቢ ክርስቲያል ከአርሰናል ይፋለማሉ።
በሙሉቀን ባሳ
More Stories
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጠው
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች