ቶትንሃም ማንቸስተር ዩናይትድን አሸንፎ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አለፈ
በእንግሊዝ የካራባው ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ቶትንሃም ማንቸስተር ዩናይትድን 4ለ3 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜው አልፏል።
የቶቴንሃምን የማሸነፊያ ግቦች ዶሚኒክ ሶላንኬ ሁለት ግቦች ሲያስቆጥር ዴጃን ኩሉስቭስኪ እና ሰን ቀሪ ግቦችን ከመረብ አሳርፈዋል።
የማንቸስተር ዩናይትድን ግቦች ጆሹዋ ዚርክዜ፣አማድ ዲያሎ እና ጆኒ ኢቫንስ አስቆጥረዋል።
ቶትንሃም ማሸነፉን ተከትሎ ከአርሰናል፣ሊቨርፑል እና ኒውካስል ቀጥሎ ግማሽ ፍፃሜውን የተቀላቀለ 4ኛው ክለብ ሆኗል።
በግማሽ ፍፃሜውም ቶትንሃም ከሊቨርፑል እንዲሁም አርሰናል ከኒውካስል ዩናይትድ ተደልድለዋል።
የግማሽ ፍፃሜው የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ታህሳስ 27/2017 ዓ.ም እና ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሄዱ ይሆናል።
በሌላ በኩል በአውሮፓ የኮንፈረንስ ሊግ የእንግሊዙ ክለብ ቼልሲ በመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታው ሻውንዶን ሮቨርስን 5ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ሁሉንም(6) የማጣሪያ ጨዋታዎች በድል በማጠናቀቅ ጥሎ ማለፉን ተቀላቅሏል።
የቼልሲን የማሸነፊያ ግቦች ማርክ ጉይ 3 ግቦችን በማስቆጠር ሃትሪክ መስራት ሲችል ማርክ ኩኩሬላ እና ዴውስበሪ ሀል ቀሪ ግቦችን አስቆጥረዋል።
በሙሉቀን ባሳ
More Stories
የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ከቶትንሃም ጋር ዛሬ የሚያከናውኑት ጨዋታ ይጠበቃል
ማንቸስተር ሲቲ በአስቶንቪላ ተሸነፈ
አስቶንቪላ ከማንቸስተር ሲቲ እንዲሁም ክርስቲያል ፓላስ ከአርሰናል ዛሬ ይጫወታሉ