ማርከስ ራሽፎርድ ማንቸስተር ዩናይትድን ሊለቅ እንደሚችል አሳወቀ
እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጫዋች ማርከስ ራሽፎርድ በመጪው የጥር ወርም ቢሆንም ማንቸስተር ዩናይትድን ለመልቀቅ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።
ባለፈው ዕሁድ በማንቸስተር ደርቢ በምዘና ከስብስቡ ውጪ የተደረገው ራሽፎርድ በክለቡ ስለወደፊት ቆይታው በሰጠው አስተያየት “ለአዲስ ፈተና ዝግጁ ነኝ ብዬ አስባለሁ” ሲል ተናግሯል።
ራሽፎርድ አክሎም “ማንቸስተር ዩናይትድን የምለቅ ከሆነ ከእኔ ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ መጥፎ ነገር አይሰማም” በማለት ከእንግሊዛዊው ጋዜጠኛ ሄነሪ ዊንተር ጋር በነበረው ቆይታ ተናግሯል።
ማንቸስተር ዩናይትድ በክለቡ ከፍተኛ ተከፋይ ከሆኑ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነውን ማርከስ ራሽፎርድን ለሌላ ክለብ አሳልፎ የመስጠት ፍላጎት አለውም ተብሏል።
ራሽፎርድ በያዝነው የውድድር ዓመት በ24 ጨዋታዎች ተሰልፎ 7 ግቦችን ሲያስቆጥር 3 ግብ የሆኑ ኳሶችን ማቀበል ችሏል።
እንደ አውሮፓዊያኑ በ2016 ለዋናው ቡድን ተሰልፎ መጫወት የጀመረው ማርከስ ራሽፎርድ እስካሁን በሁሉም ውድድሮች 426 ጨዋታዎችን አከናውኖ 138 ጎሎችን ከመረብ አሳርፏል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ሀገር አቀፍ የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ያለምንም ችግር እንዲካሄድ በቂ ዝግጅት መደረጉን የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ ገለፁ
ዳራማሎ ደንዳሾ ስፖርት ክለብ ባስኬት ቡናን በማሸነፍ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የዋንጫ አሸናፊ ሆነ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ለፍፃሜ ያለፉ ክለቦች ተለይተው ታውቀዋል