19ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአልን ለማክበር ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ወደ አርባምንጭ ከተማ የሚመጡ እንግዶች አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል
ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በአሉን ለማክበር ወደ አርባምንጭ ከተማ እየገቡ ለሚገኙ እንግዶች በጋሞ ዞን ምዕራብ አባያ ወረዳ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቢሮ ኃላፊዎች፣ የዞኑ ዋና አፈ ጉባኤ፣ የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪን ጨምሮ የብርብር ከተማ አስተዳደር እና የወረዳው የስራ ኃላፊዎች እንግዶችን ተቀብለው እያስተናገዱ ይገኛሉ።
እንግዶቹም በተደረገላቸው የሞቀ አቀባበል መደሰታቸውን ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ ገነት መኮንን – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።