‎ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ እንደሚሠራ የዲላ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ

‎ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ እንደሚሠራ የዲላ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ

‎ከተማዋን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ እንደሚሠራ የዲላ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ
‎
‎”ዳራሮ ለባህልና ለቱሪዝም ልማት” በሚል መሪ ቃል በሚከበረው የዳራሮ በዓል የ2 ነጥብ 5 ቢልዮን ብር የልማት ፕሮጀክቶች የዳራሮ ብስራቶች መርሃ ግብር ተካሂዷል።
‎
‎የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መስፍን ደምሴ (ዶ/ር)፤ ሀገራችን የበርካታ ባህልና እሴት ባለቤት መሆኗንና የሰላም፣ የፍቅርና አንድነት ነጸብራቅ የሆነው የዳራሮ በዓልም ለዚህ ማሳያ መሆኑን አመላክተዋል።
‎
‎”ዳራሮ ለባህልና ቱሪዝም ልማት” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የዳራሮ በዓልን ከልማት ጋር ለማስተሳሰር በምንሠራው ሥራ ከህዝቡ ጋር ከተማችንን ለነዋሪዎች ምቹና ውብ ለማድረግ እንሠራለን ብለዋል።
‎
‎የ5 ኪሎ ሜትር አስፓልት መንገድ፣ ባለ ሰባት ወለል የአስተዳደር ህንጻ፣ የወንዝ ዳርቻ ልማትና የከተማዋን ገጽታ የሚቀይሩ የአደባባይ ኮሪደር ፕሮጀክቶች የሚሠሩ መሆናቸዉን ተናግረዋል።
‎
‎ፕሮጀክቶቹ ከ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚፈጁ መሆናቸውን ገልጸው፤ ከህዝቡ ጋር የሚፈጸም ይሆናል ብለዋል ዶ/ር መስፍን።
‎
‎የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ፕሮጀክቶቹ ከተማዋን የቱሪዝም እና የኮንፈረንስ ማዕከል ያደርጋታል ብለዋል።
‎
‎የዲላ ከተማ ከተቆረቆረች ከ1 መቶ 20 ዓመታት በላይ ያስቆጠረች ቢሆንም በተፈለገው ልክ አለማደጓንና አሁን የሚጀመሩ ፕሮጀክቶች ከተማዋን ከፍ የሚያደርጉና በመንግስት ሀብት ብቻ የሚፈጸሙ ባለመሆናቸው በጋራ ተባብረን ዲላን ማልማት ያስፈልገናል ብለዋል።
‎
‎ዳራሮ ከባህላዊነት ባሻገር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳን እያመጣ መሆኑንም አስተዳዳሪው አመላክተዋል።
‎
‎ዘጋቢ: እስራኤል ቅጣው – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን