ህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ፍትህ ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት ሥራ አፈፃፀም አደመጠ
ሀዋሳ: ጥር 29/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ፍትህ ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት ሥራ አፈፃፀም ገምግሟል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ፍትህ ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ 6 ወራት ሥራ አፈፃፀም በዝርዝር ተመልክቷል።
የተቋሙን የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀርቡት የፍትህ ቢሮ ምክትል ሀላፊና የወንጀልና ፍትሃብሔር ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጤናው ጨርቆስ፥ በበጀት ዓመቱ 6 ወራት የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማ ለማድረግ በቅንጅት በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ አፈፃፀም መመዝገቡን ገልዋል::
የሙስና እና የታክስ ወንጀሎች በፍርድ ቤት ክስ በመመሠረት አሰተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ በትኩረት መሠራቱን የገለፁት ኃላፊው፥ የፍትህን የማረጋገጥ ስራዎች የህብረተሰቡ ተሳትፎ በማጠናከር እና በየአካባቢው ያሉ የፀጥታ ስጋቶችን ለይቶ በመፍታት የክልሉን አንጻራዊ ሰላም ማፅናትና አስተማማኝ ደረጃ ማድረስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ጠንካራ እና አስተማማኝ ተቋም በመገንባት የፍትህ ስርዓቱን በማጠናከርና አስተማማኝ ደረጃ ከማድረስ ባለፈ፥ በተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸው ገልፀዋል።
ቋሚ ኮሚቴው በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ ግልፅነትና ማብራሪያ በሚሹ ጉዳዮች ላይ ጥያቄና አስተያየት ሰጥተዋል::
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሉቀን ታደሰ ቋሚ ኮሚቴዉ ላቀረበው ጥያቄና አስተያየት ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፥ የመንግስትና የህዝብ ሃብት ያለባቸዉ የፍትሃብሔር ወንጀሎች የተሻለ አፈፃ ፀም መመዝገቡን ገልፀዋል::
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቶ ዱንጋ ናኩዋ፣ የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥ፣ ታራሚ ይቅርታ አሰጣጥ ግልኝንነት፣ ከማረም ማነጽ በተያያዘ በፍትህ ተቋማት የሚሰተዋሉ ችግሮች ለመቅረፍ በጋራ መሥራት ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ: ተስፋዬ ወ/ማሪያም

More Stories
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች በዘላቂነት እንዲመለሱ ከየትኛውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ገለፀ
መንግስት የደን ጭፍጨፋን በመከላከል የአየር ሚዛንን ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ እስታውቀ
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ እንዲያስችል ዞኑ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ