የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ስናከብር የህብረ-ብሔራዊ ቀለማት ድምቀት መሆናችንን በማሳየትና የተጋመደውን አብሮነታችንን በማጠናከር ሊሆን ይገባል – ዶ/ር ፋሪስ ደሊል
ሀዋሳ፡ ሕዳር 26/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የዘንድሮ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን ስናከብር የህብረ-ብሔራዊ ቀለማት ድምቀት መሆናችንን በማሳየትና የተጋመደውን አብሮነታችንን በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል ገለጹ፡፡
የዘንድሮ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ስናከብር የህብረብሄራዊ ቀለማት ድምቀት መሆናችንን በማሳየትና የተጋመደውን አብሮነታችንን በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል ገለፁ።
በዩኒቨርስቲው 19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በፖናል ውይይትና በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።
በበዓሉ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል የዘንድሮው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ስናከብር የህብረብሄራዊ ቀለማት ድምቀት መሆናችንን በማሳየትና የተጋመደውን አብሮነታችንን በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በሀገሪቱ ያለው የዳበረ እና በህዝቦች የአብሮነት መስተጋብር የደመቀው ህብረብሄራዊነት ለላቀ የሀገር ግንባታ መዋል እንዳለበትም ፕሬዚዳንቱ አክለዋል።
የበዓሉ መከበር የማህበረሰቡን አንድነት እና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለማጠናከር ዓይነተኛ ሚና እንደሚጫወት አስረድተዋል፡፡
በዩኒቨርስቲው የመወያያ ሰነዶች ቀርቦ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።
“ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት” በሚል መርህ እየተከበረ በሚገኘው በዓል ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል እና የዩኒቨርሲቲው የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሃንስ ገብሩን ጨምሮ ሌሎች የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ ሰራተኞችና ተማሪዎች ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ: መሐመድ ሽሁር – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
ተቀራርቦ በጋራ መሥራት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እንደሚያዝ ተጠቆመ
የጀፎረ ባህላዊ አውራ መንገድን ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ተጠቆመ
በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የማስተማር አቅም ግንባታ ለትምህርት ባለድርሻ አካላት ስልጠና ተሰጠ