ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ፤ የክልሉ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ እና የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ናፊሴ አለማህድ በጋራ በአርባምንጭ ከተማ ክልላዊ የባህልና ቱሪዝም ኤግዚቢሽን እና ፌስቲቫል በይፋ መርቀው አስጀመሩ
ሀዋሳ፡ ሕዳር 26/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እና የኢፌዲሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ናፊሴ አለማህድ በጋራ በአርባምንጭ ከተማ ክልላዊ የባህልና ቱሪዝም ኤግዚቢሽን እና ፌስቲቫል በይፋ መርቀው አስጀምረዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የኢፌዲሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ናፊሴ አለማህድ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ጸሐይ ወራሳ ጨምሮ የክልልና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፌስቲቫሉን እየጎበኙ ይገኛሉ።
በኤግዚቢሽን እና ፌስቲባሉ በክልሉ የሚገኘ 32ቱ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፤ ባህላቸውን፣ ታሪክና ቅርሳቸውን እንዲሁም የቱሪዝም ሀብቶቻቸውን ከማስተዋወቅ ባለፈ ለዘመናት የዘለቀውን ትስስራቸውን ያጠናክሩበታል ተብሏል።
“ሀገራዊ መግባባት፤ ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል 19ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በተለያዩ ሁነቶች በደማቅ ሁኔታ በአርባምንጭ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ተመኙህ ገረሱ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

                
                                        
                                        
                                        
                                        
More Stories
በትምህርት ሴክተር የመረጃ አያያዝ ውጤታማነት ዙሪያ በኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
ሁሉንም የመማሪያ መጻሕፍት ባለማግኘታቸው በትምህርታቸው ላይ ጫና እየፈጠረባቸው መሆኑን በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የቆንጋና ቆቄ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተናገሩ
ከ2 ሺህ በላይ አዲስ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን መታቀዱን የሆሳዕና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አስታወቃ