19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ያለአንዳች ፀጥታ ችግር ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ተደርጓል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን
ሀዋሳ፡ ሕዳር 25/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) 19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ያለአንዳች ፀጥታ ችግር ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት መደረጉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ኮሚሽኑ ይህንን አስመልክቶ ለሚዲያ አካላት መግለጫ ሰጥቷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍሰሀ ጋረደው በሰጡት መግለጫ፤ 19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ተከብሮ በሠላም እንዲጠናቀቅ በፀጥታ አካላት በቂ ዝግጅት መደረጉን አብራርተዋል።
በመላው ሀገሪቱ እንግዶች በዓሉን ለማክበር በሚመጡበት ወቅት የፀጥታ ችግር እንዳይኖር ከአጎራባች ክልሎች ጋርም በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
የፌደሬሽን ምክር ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ በላይ መርሻ በበኩላቸው፤ እየተከበረ የሚገኘው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በሠላም እንዲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ የፀጥታ ሀይሉ በቅንጅት እየሰራ ነው ብለዋል።
በዓሉ ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ የፀጥታ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።
ዘጋቢ፡ እንጃ ገልሲሞ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን

More Stories
ሀገራዊ ምክክር፤ የመደማመጥ፣ የመግባባትና የጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ መሠረት ነው!
ከ23 ሚሊየን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እንደሚተከሉ ተገለጸ
በግንቦት እና ሰኔ 2018 ዓ.ም ወራት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ፣ በቱሪዝም፣ በአረንጓዴ ዐሻራ፣ በዲጂታል ኢትዮጵያ፣ በሀገር በቀል ሪፎርም እና ቀጣናዊ ዲፕሎማሲ ዙሪያ ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ከፍተኛ የሥራ ክንውኖችን አድርገዋል።