አስር ሄክታር መሬት ለዲያስፖራ ኢንቨስትመንት ተዘጋጅቷል
በጌቱ ሻንቆ
በቀድሞው የደበብ ክልል የሚኖሩ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦችን የመልካም አስተዳዳርና ሌሎች ማህበራዊ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ክልሎቹን በአራት አዳዲስ ክልሎች የማደራጀት ተግባር ተከናውኗል። ከተፈጠሩት አደረጃጀቶች መካካል አንዱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ነው፡፡ በዚህ አዲስ በተደራጀው ክልል ውስጥ ባለሀብቶች ተለይተው በቀረቡ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ መእዋለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥረቶች ተደርጓል።
በ2017 በጀት ዓመት በክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ስር በሚገኙ ሁለት ዘርፎች የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል፡፡
ጥረቶቹ የሚጀምሩት የክልሉን ዕምቅ አቅሞች ከማስተዋወቅ ነው፡፡
በተያዘው በጀት ዓመት አንደኛ ሩብ ዓመት የተለያዩ የፕሮሞሽን ስልቶችን በመጠቀም ባለሀብቶችን በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ እና ወደ ክልሉ እንዲሳቡ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡
67 ባለሀብቶች በፕሮሞሽን ስራዎች በኩል እንዲሳቡ ለማድረግ ዕቅድ ተይዞ ነበር። በዚህም 67 አዳዲስ ባለሀብቶችን መሳብ ተችሏል፡፡ ባለሀብቶችን በግንባር በማግኘት ለመሳብም እንዲሁ ዕቅዶች ተነድፈው ነበር። በዚህ ጥረት 32 ባለሀብቶች ኢንቨስት እንዲያደርጉ መሳብ መቻሉን ከክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ አፈፃፀሙም ከዕቅድ በላይ መሆኑ ነው የተጠቀሰው፡፡
በሌላ በኩል ሌሎች የፕሮሞሽን ስልቶችን በመጠቀም እንደ አብነትም፤ የህትመት ሚዲያን፣ የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያን እና የስኬታማ ባለሀብቶችን ምስክርነት በመያዝ የሚደረግ የፕሮሞሽን ስራ የታሰበ ሲሆን ለአብነትም በህትመት ሚዲያ ዘርፍ ለማስተዋወቅ የተደረገው ጥረት 75 በመቶ ተፈፃሚ ሆኗል፡፡
የስኬታማ ባለሀብቶችን ምስክርነት በመጠቀም የሚደረግ የፕሮሞሽን ስልት በሚመለከት በሩብ አመቱ የታቀደው እቅድ 15 ነበር ፡፡ ነገር ግን የዕቅዱ 20 ፐርሰንት ብቻ ነው ተፈፃሚ የሆነው፡፡ አፈጸጸሙ ዝቅ ሊል የቻለው ስራው በጀት እና ሎጂስቲክ የሚጠይቅ ከመሆኑ ባሻገር ከመገናኛ ብዙሀን ጋር በመቀናጀት የሚሰራ መሆኑ ነው፡፡
በሩብ ዓመቱ በውስጥና ወይም በውጭ ከሚዘጋጁ ኢግዚቢሽኖች ጋር በመቀናጀት ለመሳተፍና ለማሳተፍ ቢታቀድም ምቹ ሁኔታዎች ባለመኖራቸው መንስዔ ተፈፃሚ አልሆነም፡፡
ሌላው በሩብ ዓመቱ ከተከናወኑት ተግባራት ተጠቃሹ ፈቃድ መስጠት፣ ማደስ፣ መለወጥ እና ማስፋፋት ናቸው። በሩብ አመቱ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና አገልግሎት ዘርፎች በጠቅላላ 67 ፈቃድ ለመስጠት ታቅዶ 67 ተከናውኗል። የፕሮጀክት ክንውኖቹ 29 በግብርና 20 በኢንዱስትሪ እና 18 በአገልግሎት ናቸው። ፈቃድ ማደስን በሚመለከት በሩብ አመቱ 50 ለማደስ ታቅዶ ክንውኑ 61 ነው። አፈጻጸሙም ከ100 ፐርሰንት በላይ ሆኗል።
ሌሎቹ አዲስ ፈቃድ የመስጠት፣ የማደስ፣ የመለወጥ እና የማስፋፋት ስራዎች ናቸው። በሩብ አመቱ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና አገልግሎት ዘርፎች በጠቅላላው 67 አዳዲስ ፈቃዶች ለመስጠት ታቅዶ 67ቱም ተከናውነዋል፡፡ እነዚህም 29 በግብርና፣ 20 በኢንዱስትሪ እና 18 በአገልግሎት ዘርፍ ናቸው፡፡ በሩብ አመቱ 50 ፍቃዶችን ለማደስ ታቅዶ 61ዱን ማደስ ተችሏል፡፡
ስድስት የስራ ፈቃድ ለውጦች ተደርገዋል። የማስፋፊያ ፈቃድን በሚመለከት በሩብ አመቱ 4 የማስፋፊያ ፈቃዶችን ለማሻሻል የታቀደ ቢሆንም የተከናወነው 1 ብቻ ነው፡፡ በሩብ አመቱ ከተሰጡ ፈቃዶች ብር በቢሊየን 3 ነጥብ 55 ካፒታል እንደሚመዘገብ ታቅዶ 3 ነጥብ 65 ቢሊየን ብር ተመዝግቧል። የሚፈጠር የስራ እድልን በሚመለከት በሩብ አመቱ ፈቃድ ያወጡት ፕሮጀክቶች ሲተገበሩ ለ9 ሺህ 295 ዜጎች ቋሚና ጊዚያዊ የስራ እድሎች እንደሚፈጥሩ ይጠበቃል፡፡
በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵውያን መንግስት በፈጠረው ምቹ ሁኔታ በተለያዩ የኢንቨሰትመንት ዘርፎች በመሰማራት በትውልድ ሀገራቸው አቅም በፈቀደና ባልተመቻቹ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነውም የማይናቅ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡
ሆኖም እስካሁን ያለው የተሳተፎ እንቅስቀሴ ዲያስፓራው ካለው እምቅ አቅምና ፍላጎት አንፃር ሲታይ እንዲሁም ሀገራችንም ትሁን ክልሉ ከዲያስፖራው፣ መጠቀም ከሚገባቸው አቅም አኳያ ሲመዘን የእስካሁኑ ጥረት በሚፈለገው ደረጃ ላይ የደረሰ አይደለም ይላል ከቢሮው የተገኘው ሪፖርት።
ዲያስፖራው በኢንቨስትመንት እንዲሳተፍ የሚያበረታቱ እና ሁሉንም የዳያስፖራ አቅሞች የሚጋብዙ አሰራሮች በመዘርጋትና ለዲያስፖራው በተለዩ ምቹ የቢዝነስ ከባቢዎችን መፍጠር እንደሚገባም ነው ዲያስፖራን የተመለከተው የቢሮው ሪፖርት የሚያትተው፡፡
በዚህም በዲያስፖራው ዘንድ ያለውን እምቅ አቅም ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያግዙ ማሻሻያዎችን ለማስተዋወቅና ተሳትፎውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያግዙ አማራጭ ፓኬጆችን ማዘጋጀት ተችሏል፡፡
የተቀረጸው ፓኬጅ የሚመለከታቸው አካላት እንዲገመግሙት እና አስተያየት እንዲሰጡበት ተደርጎ ፀድቋል፡፡ ለዚሁ ማስፈፀሚያ የሚሆን 10 ሄ/ር መሬት በዚህ ሩብ አመት እንዲዘጋጅ ታቅዶ፥ 10ሩም ሄ/ር ተዘጋጅቷል፡፡ ሌላው ቀደም ሲል ወደ ክልሉ የተሳቡ ዲያስፖራ ባለሀብቶች ምዝገባ በፕሮጀክት አይነት፣ ካፒታል እና የሚኖሩበት ሀገር መረጃ ተደራጅቷልም ይላል የቢሮው የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም፡፡
More Stories
“ኩርፊያ እና ንትርክ አልወድም” – ጋዜጠኛ ገናናው ለማ
በ2030 ደህንነቱ የተጠበቀ መጸዳጃ ቤት ለሁሉም
ኮንፈረንስ ቱሪዝም