ማርከስ ራሽፎርድ ጉዳት አጋጥሞታል
የባርሴሎና የፊት መስመር ተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ ጉዳት እንዳጋጠመው ይፋ ተደርጓል።
እንግሊዛዊው ተጫዋች ማርከስ ራሽፎርድ ባሳለፍነው ቅዳሜ ከማዮርካ ጋር በተካሄደው የላሊጋ ጨዋታ ላይ የግራ ጉልበት ጉዳት እንደገጠመው ተገልጿል።
ይህንንም ተከትሎ ራሽፎርድ ባርሴሎና ነገ ከአትሌቲኮ ማድሪድ የሚያደርገው የኮፓ ዴላሬ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ እንደሚያመልጠው አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ተናግረዋል።
እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ በሚቆይ የውሰት ውል ከማንቸስተር ዩናይትድ ባርሴሎናን የተቀላቀለው ራሽፎርድ ለስፔኑ ክለብ በሁሉም ውድድሮች እስካሁን 34 ጨዋታዎችን አከናውኗል።
የ28 ዓመቱ ተጫዋች በነዚህ ጨዋታዎች ለብሉግራናዎቹ 10 ጎሎችን ሲያስቆጥር 13 ጎል የሆኑ የመጨረሻ ኳሶችን ማቀበል ችሏል።
ባርሴሎና በነገው ጨዋታ በማርከስ ራሽፎርድ በተጨማሪ ራፊንኚያን ግልጋሎት እንደማያገኝ ማርካ አስነብቧል።
ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጫዋች በመጪው ሰኞ በካታላን ደርቢ ከጂሮና ጋር በሚደረገው የላሊጋ ጨዋታ ይሰለፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡ሙሉቀን ባሳ

More Stories
8 ወራትን ብቻ በሰሜን ለንደን የቆየው አሰልጣኝ
ማንቸስተር ዩናይትድ ቶትንሃምን አሸነፈ
አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉይ መልቀቂያ አስገቡ