በየጊዜው እየተከሰተ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት የሚያደርሰውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከል የመንገድ ዳር የትራፊክ ምልክቶች ወሳኝ ናቸው – በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ ዲስትሪክት
ሀዋሳ፡ ሕዳር 25/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በየጊዜው እየተከሰተ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት የሚያደርሰውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከል የመንገድ ዳር የትራፊክ ምልክቶች ወሳኝ መሆናቸውን በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ ዲስትሪክት አስታወቀ፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች ተለይተው የቢልቦርድ ተከላ ሥራዎች መከናወናቸውም ተገልጿል።
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ኔትዎርክ የመንገድ ደህንነት ወሰን ማስከበርና የክብደት ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ ሙሉቀን አበራ፤ የሚከሰተውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከል የመንገድ ዳር የትራፊክ ምልክቶች ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸው በተደጋጋሚ አደጋ የሚከሰትባቸውን ቦታዎች ለይተው ወደ ሥራ መግባታቸውን ተናግረዋል።
የህይወት መጥፋት እና የንብረት ውድመት እንዳይከሰት አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ታሳቢ በማድረግ የትራፊክ ምልክቶች ተከላ ማከናወናቸውን ተናግረዋል።
በአካባቢው ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችም ከተተከሉ የትራፊክ ምልክቶች ግንዛቤ በመውሰድ አደጋውን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደረጉ አሳስበዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ የመንገድ ደህንነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ዳካኖ፤ በክልሉ የትራፊክ አደጋ ከሚበዛባቸው ዞኖች መካከል የጌዴኦ ዞን አንዱ መሆኑን አንስተዋል።
በጌዴኦ ዞን ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ምክትል እና የትራንስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኤርምያስ አብዲዩ፤ በዞኑ በተደጋጋሚ አደጋ የሚከሰትበትንና ለወደፊት አደጋ ይከሰታል ተብሎ የሚታሰብባቸውን ቦታዎች በመለየት ቢልቦርድ የመትከል ሥራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።
ቢልቦርዱ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ሻሸመኔ ዲስትሪክት ድጋፍ የተደረገ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ በቀጣይ የፍጥነት መቀነሻ ብሬከሮችን ጨምሮ ሌሎችም አደጋን የመከላከል ሥራዎች እንደሚከናወኑ ተናግረዋል።
መንገድ ዳር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በመውጫ ሰዓት የሚለቀቁ ተማሪዎች የአደጋው ሰለባ ሊሆኑ ስለሚችሉ የግራ ጠርዝ መንገድ ብቻ በመጠቀም መጓዝ እንዳለባቸው ያሳሰቡት የጌዴኦ ዞን ትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር እና አደጋ መከላከል ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ታምሩ ሸጠነ፤ እግረኞችም በተመሳሳይ መንገዱን ሲያቋርጡ ግራና ቀኝ በማየት የትራፊክ አደጋን እንዲከላከሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ: አሀዱ አሸናፊ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

                
                                        
                                        
                                        
                                        
More Stories
እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ሥራ ከዳር ለማድረስ በሚደረገው ርብርብ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሙዱላ ከተማ አስተዳደር ገለፀ
በትምህርት ሴክተር የመረጃ አያያዝ ውጤታማነት ዙሪያ በኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
ሁሉንም የመማሪያ መጻሕፍት ባለማግኘታቸው በትምህርታቸው ላይ ጫና እየፈጠረባቸው መሆኑን በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የቆንጋና ቆቄ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተናገሩ