ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ችግሮችን ለመቋቋም መሠል ልማታዊ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ወ/ሮ መነቴ ሙንዲኖ ገለጹ፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ሱፐር ቭዥን ቡድን በቀቤና ልዩ ወረዳ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ማእቀፍ ለመሻገር እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን አስመልክቶ የመስክ ምልከታ አድርጓል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ መነቴ ሙንዲኖ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት፤ የመስክ ምልክታው አላማ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚል መሪ ቃል በልዩ ወረዳው ምርታማነትን በማሳደግ በራስ አቅም ራስን ለመቻል እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ለመቃኘት ነው።
ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ችግሮችን ለመቋቋም መሠል ልማታዊ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ያሉት ምክትል አፈ ጉባኤዋ በልዩ ወረዳው በሪዮ ቀበሌ በ20 ሄክታር ማሳ ላይ የለማው ሰብል በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑን በመስክ ምልከታው ማረጋገጥ መቻላቸውን ገልፀዋል።
ከሰብል ልማቱ ከ1ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል ያሉት ምክትል አፈ ጉባኤዋ ይህንን ተሞክሮ ወደ ሌሎችም የክልሉ አከባቢዎች በማስፋት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባ አመላክተዋል።
የቀቤና ልዩ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አቡበከር ዱላ በበኩላቸው፤ ተረጂነት አንገት የሚያስደፋና የሀገርን ገፅታ የሚያበላሽ ክስተት መሆኑን ጠቁመው ይህንን እሳቤ ለመከላከል በተደረገው ጥረት አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን አስረድተዋል።
በተለይ በምግብ ሰብል ፍጆታ ራስን ለመቻል በልዩ ወረዳው በግብርናው ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት አመርቂ መሆናቸውን አቶ አቡበከር ተናግረዋል።
ለህብረተሰቡ የሚደረገውን ሰብአዊ ድጋፍ ለማሻሻልና ሊከሰቱ የሚችሉትን ችግሮች በራስ አቅም ለመሸፈን በባሪዮ ቀበሌ በ20 ሄክታር የለማው ሰብል በአግባቡ ሰብስቦ ለመጠቀም በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ በልዩ ወረዳው ያሉ ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል ያሉት ኃላፊው በተለይ የበጋ መስኖ እርሻ ልማት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ገልፀዋል።
በቀቤና ልዩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የአዝእርት ልማት ድህረ ምርት ቴክኖሎጂ ባለሙያ አቶ አብድልሀይ አብድልጀልል፤ ከዚህ በፊት በልዩ ወረዳው ያለ አገልግሎት የተቀመጡ በርካታ ስፍራዎች ለእርሻ አገልግሎት እንዲውሉ በማድረግ የምርታማነት አቅምና ጥራትን ማሳደግ መቻሉን ተናግረዋል።
ከመደበኛ የእርሻ ተግባር በተጨማሪ በበጋ መስኖ እርሻ ልማት እየተሰሩ ያሉ ልማታዊ ተግባራት የአርሶ አደሩን ብልፅግና ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና እንዳላቸው ባለሙያዊ ገልፀዋል።
የበሪዮ ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ ሰፋ አለሙ፤ በቀበሌው ለአደጋ መከላከል ታስቦ የለማው ሰብል ለቀበሌው ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ተደራሽ መሆን ለማድረግ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
አላማው በጎ እሳቤ ያለውና ለህብረተሰቡ ሰብአዊ ሰብአዊ ድጋፍን በአፋጣኝ ተደራሽ ለማድረግ ምቹ እድል የሚፈጥር በመሆኑ በቀጣይ በተሻለ ሁኔታ ህብረተሰቡን በንቃት በማሳተፍ እንደሚሰሩ ሊቀመንበሩ አመላክተዋል።
ዘጋቢ፡ አስቻለው ተስፋዬ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ያለአንዳች ፀጥታ ችግር ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ተደርጓል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን
ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎች በኃላፊነት ሊሰሩ እንደሚገባ የኣሪ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ማዕከል ከአለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በክልሉ ከምባታ ዞን ዶዮገና ወረዳ የጀመረው የትሮፒካል የዶሮ ዝርያ ማሻሻያ ፕሮጀክት ውጤታማ እንዳደረጋቸው በፕሮጀክቱ የታቀፉ አርሶ አደሮች ተናገሩ