የቡርጂ ዞን ሶያማ ከተማ የበጋ በጎ ፈቃድ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በተለያዩ ስፖርታዊ ዝግጅቶች ተጀመረ
ሀዋሳ፡ ሕዳር 23/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቡርጂ ዞን ሶያማ ከተማ የበጋ በጎ ፈቃድ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በተለያዩ ስፖርታዊ ዝግጅቶች ተጀምሯል፡፡
ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የሶያማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ፍስሃ አድማሱ ባደረጉት ንግግር፤ የከተማው ወጣት የአካል ብቃቱን እና የስፖርት ችሎታውን ለማሳደግ በስፖርታዊ ውድድሮች ላይ መሳተፍ እንዳለበት አመላክተዋል።
በሶያማ ከተማ ደረጃ ብቁ እና በስነ-ምግባር የታነፀ ወጣት ለማፍራት ቃል መገባቱን ያስታወሱት ከንቲባው፤ ውድድሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከተማ አስተዳደሩ ምቹ ሁኔታ የመፍጠሩን ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።
በበጋ ወቅት ከሚሰሩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መካከል አንዱ የሆነው የእግር ኳስ ጨዋታ በአጠቃላይ በአዋቂ 4 በታዳጊ 6 በድምሩ 10 ቡድኖች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ታውቋል።
በመርሃ ግብሩ የዞን፣ የሶያማ ዙሪያ ወረዳ እንዲሁም የሶያማ ከተማ አስተዳደር አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታዳሚ ሆነዋል።
ዘጋቢ፡ ወርቅአገኘሁ ወልደየስ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ተቀራርቦ በጋራ መሥራት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እንደሚያዝ ተጠቆመ
የጀፎረ ባህላዊ አውራ መንገድን ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ ተጠቆመ
በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የማስተማር አቅም ግንባታ ለትምህርት ባለድርሻ አካላት ስልጠና ተሰጠ