በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 19ኛዉ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ክልላዊ የማጠቃለያ ፕሮግራም እየተካሄደ ነዉ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 19ኛዉ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ክልላዊ የማጠቃለያ ፕሮግራም እየተካሄደ ነዉ

ሀዋሳ፡ ሕዳር 23/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 19ኛዉ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ክልላዊ የማጠቃለያ ፕሮግራም በክልሉ የብሔረሰቦች ምክር ቤት መቀመጫ በሆነዉ የም ዞን ሳጃ ከተማ እየተከበረ ነዉ።

በበዓሉ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻዉ ጣሰዉ፣ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣ የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና ልዩ ወረዳ አመራሮች፣ የአጎራባች ክልል ተወካዮች፣ የሐይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል፡፡

ዘጋቢ፡ ድልነሳዉ ታደሰ