ለውጡና የለውጡ ፍሬዎች !!!
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ
ብልጽግና ፓርቲ ነባሮቹን ፖለቲካዊ ዕሤቶች በሚያጎለብትና የፖለቲካ ስብራቶቻችንን በሚጠግን መልኩ ተመሥርቷል፡፡ ይሄም የለውጡ አንዱ ፍሬ ነው፡፡
የብልጽግና መመሥረት የዳርና የመሐል፤ ዋና እና አጋር፣ አርብቶ አደርና አርሶ አደር፤ ተራማጅና አድኃሪ፤ ጠላትና ወዳጅ፣ ወዘተ. የሚባሉትን ግንቦች በማፍረስ በሐሳብ ላይ ብቻ የተመሠረተ የፖለቲካ አደረጃጀትን ፈጥሯል፡፡
የሐሳብ ልዩነቶችን እንደ ጌጥና ዕሴት በመውሰድ ተፎካካሪዎቹን በጠላትነት አይፈርጅም፡፡ በኢትዮጵያዊ ዕሴቶች ላይ በመመሥረት፣ ከሌሎች ሐሳቦች በመማር፣ በገቢር ነበብ መንገድ ይጓዛል እንጂ የርዕዮተ ዓለም እሥረኛ አይደለም፡፡
ለአንድ አካባቢ ወይም ብሔር የቆመ ሳይሆን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ያለው የሐሳብ ፓርቲ ነው፡፡ ይሄም የኢትዮጵያን የፖለቲካ መልክአ ምድር የለወጠ የለውጥ ፍሬ ነው፡፡
More Stories
የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ #ደሬቴድ፣ ሐምሌ 07/2017 ዓ.ም
የጤናው ዘርፍ አገልግሎት ለማጠናከር የግብረ ሰናይ ድርጅቶች ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ
የኮሪደር ልማት ሥራዎች የሕብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ እየቀየረ መምጣቱን ነዋሪዎች ተናገሩ