ለውጡና የለውጡ ፍሬዎች
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የብልጽግና መመሥረት፡ የኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታሪክ ነው፡፡
እነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖለቲካ ንቃት በማኅበረሰቡ ውስጥ እንዲፈጠር አድርገዋል፡፡ የፖለቲካ አደረጃቶችን አምጥተዋል፡፡
የሕዝብ ጥያቄዎችን ቅርጽና መልክ ሰጥተዋል፡፡ የፖለቲካ ትግል ስልቶችንም አስተዋውቀዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የትጥቅ ትግልና የፖለቲካ ትግል እንዲቀላቀል፤ የጥላቻ ፖለቲካ እንዲነግሥ፣ በብሔር፣ በርዕዮተ ዓለምና በትግል ስልት መፈራረጅ እንዲበረታ በማድረግ ለዘመናዊ የፖለቲካ ጉዟችን ሳንካዎችን አኑረዋል፡፡
ብልጽግና ፓርቲ ነባሮቹን ፖለቲካዊ ዕሤቶች በሚያጎለብትና የፖለቲካ ስብራቶቻችንን በሚጠግን መልኩ ተመሥርቷል፡፡
ይሄም የለውጡ አንዱ ፍሬ ነው፡፡ የብልጽግና መመሥረት የዳርና የመሐል፤ ዋና እና አጋር፣ አርብቶ አደርና አርሶ አደር፤ ተራማጅና አድኃሪ፤ ጠላትና ወዳጅ፣ ወዘተ. የሚባሉትን ግንቦች በማፍረስ በሐሳብ ላይ ብቻ የተመሠረተ የፖለቲካ አደረጃጀትን ፈጥሯል፡፡
የሐሳብ ልዩነቶችን እንደ ጌጥና ዕሴት በመውሰድ ተፎካካሪዎቹን በጠላትነት አይፈርጅም፡፡ በኢትዮጵያዊ ዕሴቶች ላይ በመመሥረት፣ ከሌሎች ሐሳቦች በመማር፣ በገቢር ነበብ መንገድ ይጓዛል እንጂ የርዕዮተ ዓለም እሥረኛ አይደለም፡፡
ለአንድ አካባቢ ወይም ብሔር የቆመ ሳይሆን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ያለው የሐሳብ ፓርቲ ነው፡፡ ይሄም የኢትዮጵያን የፖለቲካ መልክአ ምድር የለወጠ የለውጥ ፍሬ ነው፡፡

More Stories
የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጥምረት የፍትህ አሰጣጥ ላይ ውጤታማ ማድረጉ ተገለጸ
አቶ ዮሐንስ አበጋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።