በአመራሩና በፈጻሚ ደረጃ ላይ ያሉ ተግባራትን በተነሳሽነት በመስራት እና በጤናው ዘርፍ ያሉ ጉድለቶችን በመለየት ፈጣን እና ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት ይገባል – የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ

በአመራሩና በፈጻሚ ደረጃ ላይ ያሉ ተግባራትን በተነሳሽነት በመስራት እና በጤናው ዘርፍ ያሉ ጉድለቶችን በመለየት ፈጣን እና ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት ይገባል – የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ

ሀዋሳ፡ ሕዳር 21/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በአመራሩና በፈጻሚ ደረጃ ላይ ያሉ ተግባራትን በተነሳሽነት በመስራት እና በጤናው ዘርፍ ያሉ ጉድለቶችን በመለየት ፈጣን እና ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ የእናቶች እና ህጻናት ጤናና ስርዓተ ምግብ አገልግሎት የ2017 ዓ/ም የመጀመሪያ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አካሂዷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል እና የበሽታ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ በአመራሩና በፈጻሚ ደረጃ ያሉ ተግባራትን በተነሳሽነት በመስራት በጤናው ዘርፍ ያሉ ጉድለቶችን በመለየት ፈጣን እና ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ገልፀዋል።

የህብረተሰቡ ጤና እንዲሻሻል በተለይም የናቶችና የህጻናት ሞትን ለመቀነስ አገልግሎቱን ማዘመን እንደሚያስፈልግ በማንሳት በጤናው ዘርፍ በተያዘው የሩብ አመት የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡን ምክትል ሃላፊው ጠቁመዋል።

የህጻናት የክትባት አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ ረገድ ተስፋ ሰጪ ውጤት ቢመዘገብም በጥራት ከመስጠት አኳያ ጠንካራ ክትትል በማድረግ የሚታይ ለውጥ ማምጣት ይገባልም ብለዋል አቶ አሸናፊ።

የቅድመ ወሊድ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ክፍቶችን በመለት አፋጣኝ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ማመላከት ወሳኝ መሆኑንም አስረድተዋል።

በመድረኩ የ2017 የሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በክልሉ ጤና ቢሮ የእናቶችና ህፃናት ጤና እና ስርአተ ምግብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ተስፋዬ ሌጂሶ ቀርቧል።

በዚህም በክልሉ በሁሉም መዋቅሮች የእናቶች እና ህፃናት ጤና ከመጠበቅ፣ ከቅድመ ወሊድ ክትትል ከማድረግ እንዲሁም ከስርአተ ምግብ አገልግሎት አሰጣጥ አኳያ ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ውጤት መመዝገቡን አስረድተዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የጤናው ዘርፍ እናቶች የቤትሰብ እቅድ አገልግሎት በተሟላ መልኩ እንዲጠቀሙ ግንዛቤ መፍጠር እና የእናቶችና ህጻናት ሞትን መቀነስ ዋና ዋና ተግባራቱ በመሆናቸው ለውጥኑ መሳካት በርካታ ተግባራት ማከናወናቸውን ተናግረዋል።

በቀጣይም በሩብ አመቱ አፈፃፀም ወቅት እንደ ውስንነት የተለዩ ተግባራትን በመለየት የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንደሚሰሩም አስተያየት ሰጪዎቹ ጠቁመዋል።

ዘጋቢ፡ አስቻለው አማረ – ከወልቂጤ ጣቢያችን