ሀዋሳ፡ ሕዳር 18/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) 19ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ሲያከብሩ አንድነታቸውን በማጠናከር እና ሰላማቸውን በማስጠበቅ እንደሆነ የምእራብ ኦሞ ዞን የበአሉ ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡
19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን “ሀገራዊ መግባባት፤ ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች በምእራብ ኦሞ ዞን ተከብሯል።
በአርብቶ እና ከፊል የአርሶ አደር ወረዳዎች የሚታወቀውና የሱርማ፣ መኢኒት፣ ዲዚ እና ዚልማሞ ብሔረሰቦችን አቅፎ የያዘው የምእራብ ኦሞ ዞን፤ በርካታ ባህላዊ እሴቶች እና ሀብቶች ያሉት አካባቢ ቢሆንም ለብዙ ዘመናት ወደፊት ሳይወጣ መቆየቱን ነው በ19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአል በምእራብ ኦሞ ዞን ሲከበር በበአሉ ላይ የተሳተፉ ተሳታፊዎች የተናገሩት።
ተሳታፊዎቹ በተለይም የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ማክበራቸው ማንነታቸውን ከማስተዋወቅ ባለፈ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ባህል አና የአኗኗር ዘይቤ ልምድ መቅሰም መቻላቸውን ጠቁመዋል።
ተሳታፊዎቹ አክለውም በአሉን ሲያከብሩ አንድነታቸውን በማጠናከር ሰላማቸውን በማስጠበቅ እንደሆነም ጠቁመዋል።
በበአሉ የጥያቄ እና መልስ ውድድር የተካሄደበት ሲሆን የውድድሩ ተሳታፊዎች ስለ ብሔረሰቦች ማንነት እና ስለ ህገ መንግስት በትምህርት ቤታቸው ከሚሰጣቸው ትምህርት በዘለል በበዓሉ መሳተፋቸው ተጨማሪ እውቀት እንዲጨብጡ እንዳደረጋቸው ጠቁመዋል።
የምእራብ ኦሞ ዞን ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ቢልልኝ ወልደሰንበት እንዳሉት፤ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን መከበሩ በሀገሪቱ ያሉ ብሔር ብሔረሰቦች የየራሳቸውን መብት እና ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ያረጋግጡበት እለት በመሆኑ እለቱን ልዩ ያደርገዋል።
ጉድለቶችን በማረም አንዱ የሌላውን ሰብአዊ ዲሞክራሲያዊ መብት የመቀበል የማክበር ባህልን በማሳደግ ነጠላ ትርክቶችን ወደ ወል ትርክቶች በመቀየር ገዢ ቦታ እንዲይዝ በትኩረት መስራት ይገባልም ብለዋል።
የምእራብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ተወካይ እና የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሼማጂ ጉርጩማ በበኩላቸው፤ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን የህዝቦች እኩልነት የተረጋገጠበት፣ ባህል እና እሴቶቻቸውን ወደ ፊት እንዲወጡ ያደረጉበት ልዩ ቀን በመሆኑ በድምቀት እንደተከበረ ጠቁመዋል።
በአሉን ሲያከብሩም ይበልጥ የህዝቦች አብሮ የመኖር እሴቶቻቸው የሚዳብርበት ዘላቂ ሰላም ይበልጥ የሚጎለብትበት ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ፡ አብዮት በቀለ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
19ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት በሚል መሪ ሀሳብ በማረቆ ልዩ ወረዳ በድምቀት ተከበረ
በተግባር የተደገፈ ትምህርት የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበርክት ተገለጸ
ከደረሰኝ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የሚስተዋለውን ችግር ለመፍታት የነጋዴው ማህበረሰብ ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ እንደሚገባ ተጠቆመ