በመኸር እርሻ ከተዘራው ሰብል 53 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ወደ ጎተራ ገብቷል
በ2016/17 ዓ.ም በምኸር እርሻ በዘር ከተሸፈነ 20 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ከሰባት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ምርት የመሰብሰብ ስራ ተሰርቷል።
ከተሰበሰበው ሰባት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሄክታር መሬት 53 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ወደ ጎተራ ገብቷል።
በግብርና ሚኒስቴር የሰብል ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ኢሳያስ ለማ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በ2016/17 መኸር እርሻ በዘር ከተሸፈነ 20 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ውስጥ ሰባት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ያለወ ሰብል ተሰብስቧል። ከዚህም 53 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ወደ ጎተራ ገብቷል፡፡
በዘር ከተሸፈነ 20 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ውስጥ 12 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ያለው ሰብል ለመሰብሰብ ደርሷል ያሉት መሪ ስራ አስፈፃሚው ከዚህም ስድስት ነጥብ ስምንት ሚሊየን በሰው ሀይል፤ 360 ሺህ ሄክታሩን በኮባይነር የመሰብሰብ ስራ ተከናውኗል፡፡ ወደ አምስት ሚሊዮን የሚጠጋ ሄክታር መሬት አለመሰብሰቡን ገልጸዋል።
ከ2016/17 ዓም የምኸር እርሻ 615 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቀም ጠቁመዋል፡፡
More Stories
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ በ85 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ የነዳጅ ማዳያ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
በኃይለማሪያምና ሮማን ፋውንዴሽን አዘጋጅነት በደቡብ ኦሞ ዞን ያሉ የአርብቶ አደር ማህበረሰቦችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ውይይት በቱርሚ ከተማ እየተካሄደ ነው
የምግብ ዋስትና ዘላቂነትን ለማረጋገጥ የሌማት ትሩፋት ስራዎችን ከስራ እድል ፈጠራ ጋር በጥምረት እየተሰራ ነው – የጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ