የትምህርት ቤት አመራሮች ትውልድን በመቅረጽም ሆነ የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ ረገድ የማስተባበር፣ ክትትልና ድጋፍ የማድረግና አስተማማኝ የሆነ የክፍል ውስጥ ትምህርትና ውጤት እንዲመዘገብ በትኩረት እንዲሰሩ ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው አሳሰቡ
ሀዋሳ፡ ሕዳር 17/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የትምህርት ቤት አመራሮች ትውልድን በመቅረጽም ሆነ የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ ረገድ የማስተባበር፣ ክትትልና ድጋፍ የማድረግና አስተማማኝ የሆነ የክፍል ውስጥ ትምህርትና ውጤት እንዲመዘገብ በትኩረት እንዲሰሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው አሳስበዋል።
በክልሉ ለሚገኙ የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራኖች “የትምህርት ቤት አመራሮች ብቃት፤ ለላቀ የትምህርት ጥራት” በሚል መሪ ሀሳብ የአቅም ግንባታ ስልጠና በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ መሰጠት ተጀምሯል።
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው አክለውም የትምህርት አመራሮች የትምህርት ስብራትን ለማሻሻል እየተተገበረ ያለውን የትምህርት ጥራት ማሻሻያ በተገቢው በተግባር በማዋል የትውልድ ግንባታ ላይ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
በአቅም ግንባታ ስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪና የብልጽግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ፣ የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዳዊት ሃዬሶ እንዲሁም ሌሎች አካላት ተገኝተዋል።
የአቅም ግንባታ ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
ዘጋቢ: ወንድወሰን ሽመልስ
More Stories
የኣሪ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ድሽታ ግና በዓል በተለያዩ መርሃ-ግብሮች እየተከበረ ይገኛል
ሕዳር 29 የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በጋራ በመሆን በባህልና እሴቶቻቸው ደምቀው በአንድነት የሚያከብሩት ልዩ ቀን ነው – የኮሬ ዞን አስተዳደር
“የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በጎፋ ዞን ሣውላ ከተማ ተከበረ