ማክስ ዳውማን ከአርሰናል ጋር የስኮላርሺፕ ውል ተፈራረመ
እንግሊዛዊው ታዳጊ ተጫዋች ማክስ ዳውማን ከአርሰናል ጋር የስኮላርሺፕ ውል ተፈራርሟል።
የመስመር ተጫዋቹ በቅርቡ 16 ዓመት ስለሞላው የስኮላርሺፕ ኮንትራት የተፈራረመ ሲሆን በቀጣይ ዓመት ታህሳስ ወር ላይ 17 ዓመት ሲሆነው የመጀመሪያውን የፕሮፌሽናል ውል ይፈራረማል ተብሎ ይጠበቃል።
በ15 ዓመቱ ለመድፈኞቹ ዋናው ቡድን ተሰልፎ መጫወት የቻለው ዳውማን ከቡድን አጋሩ ኤታን ንዋኔሪ በመቀጠል በፕሪሚዬር ሊጉ መጫወት የቻለ ሁለተኛው በዕድሜ ትንሹ ተጫዋች ነው።
አሁን ላይ በጉዳት ምክንያት ከጨዋታ ርቆ የሚገኘው ማክስ ዳውማን ለአርሰናል እስካሁን በቨ5 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ ተጫውቷል።
ዘጋቢ ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።