7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና የሴቶች ሩጫ በሀዲያ ዞን በሆሳዕና ከተማ ተካሄደ
የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድሩ “ምርጫው ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊና ተዓማኒ እንዲሆን የሴቶች ሚና ከፍተኛ ነው” በሚል መሪ ሃሳብ ነው መነሻውን ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ አድርጎ የተጀመረው።
በጠቅላላ ምርጫው ላይ የሴቶች እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲሁም ዲሞክራሲ እንዲጎለብት እንደሚያደርግ በመርሀ ግብሩ ተገልጿል።
በተካሄደው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር አሸናፊ ለሆኑ ሴቶችና አትሌቶች የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ገነት ስዩም፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ብሌን ገ/መድህን፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ፋጡማ ተሰማ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ነጋሽ ገቡሬ፣ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሽጉጤ፣ የክልል፣ የዞን እና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ሌሎች የስፖርት ቤተሰቦች ተገኝቷል።
ዘጋቢ: ታምራት ዓለሙ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ አስፈረመ
ማንቸስተር ዩናይትድ አንድሬ ሳንቶስን አስፈረመ
የ2018 የCBE የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በማሸነፍ ሁለት ዋንጫ ላነሳው የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ክልሉ ያዘጋጀውን የዕውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 06/2018 ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ይካሄዳል።