ኢትዮጵያ እየገጠማት ካለው ፈተና ወጥታ ልጆቿን በእኩልነት እንድትጠቅም ሁላችንም የዜግነት አደራ አለብን – በጌዴኦ ዞን የዲላ ዙሪያ ወረዳ አሰተዳደር
ሀዋሳ፡ ሕዳር 17/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ኢትዮጵያ እየገጠማት ካለው ፈተና ወጥታ ልጆቿን በእኩልነት እንድትጠቅም ሁላችንም የዜግነት አደራ አለብን ሲል በጌዴኦ ዞን የዲላ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር አስታውቋል።
19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በወረዳው በደማቅ ሥነ ሥርዓት በተከበረበት ወቅት የዲላ ዙሪያ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ታሪኩ ታደሰ እንዳሉት ሀገራዊ መግባባት ሊፈጥሩ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ቀኑን ማክበር ይገባል፡፡
ሀገራዊ መግባባት የሚመጣው ሁላችንም ከራሳችን፣ ከቤተሰባችን እና ከፈጣሪያችን ጋር መስማማት ስንችል ነው ያሉት አቶ ታሪኩ፤ አንድነታችንን በማጠናከር ሀገራችን ኢትዮጵያ እያጋጠማት ያለውን ፈተና በድል እንድትሻገር ሁላችንም የዜግነት አደራችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
የዲላ ዙሪያ ወረዳ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አስፋው ሽብሩ፤ ህዳር 29 የብሔር ብሔረሰቦች የማንነት ጥያቄ መልስ ያገኘበት እና በልዩነቶች ውስጥ ያለው የአንድነት ብርሃን ለዓለም የበራበት ዕለት በመሆኑ በልዩ ትኩረት እንደሚከበር አስታውቀዋል፡፡
የዘንድሮው 19ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በአዲስቷ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ ህዳር 29 ይከበራል፡፡
ዘጋቢ፡ ሳሙኤል በቀለ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
አካል ጉዳተኞች መብቶቻቸውና ጥቅሞቻቸውን ለማስጠበቅ በቅንጅትና በጥምረት መስራት እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለፀ
አካባቢን በመጠበቅና በማጽዳት ምቹና ጽዱ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ሁሉም የድርሻውን ልወጣ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ አሳሰቡ
ግለሰባዊ ነጠላ ትርክቶችን በጋራ በመታገል በመደመር እሳቤ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ተገለጸ