አገርን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን ማጠናከርና የልማት ተደራሽነትን እውን ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ

አገርን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን ማጠናከርና የልማት ተደራሽነትን እውን ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ሕዳር 17/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) አገርን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ሁሉንም የሚያሣትፍ የልማት ተደራሽነትን እዉን በማድረግ ተጨባጭ ዉጤት ማስመዝገብ መቻሉም ተገለፀ።

የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልና ዞናዊ ማጠቃለያ መድረክ በተለያዩ ሁነቶች በጂንካ ከተማ ተከብሯል።

አገራዊ አንድነትንና አብሮነትን በማጠናከር መልካም እሴቶችን በማጎልበት የሚስተዋሉ የአሠራር ችግሮችን በመፍታት የአገር ብልፅግናን ከፍ ማድረግ የሚያስችሉ ዘርፈብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ በመድረኩ ንግግር ያደረጉት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር አበባየሁ ታደሰ ገልጸዋል ።

የብልጽግና ፓርቲ ሁሉንም አካታችና አገርን ወደ ላቀ ከፍታ ለማሻገር ሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር፣ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን የተሻለ ዉጤት ማስመዝገብ የተቻለበት፣ የትምህርት ሥራዎችን ለማሻሻልና ብቁ ዜጋ ለመፍጠር ሁሉአቀፍ አሠራር መዘርጋት የተቻለበትን አጋጣሚ ፈጥሯል ብለዋል።

ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሆኑ ከማድረግ አኳያ ተጨባጭ ለዉጥና እድገት ማምጣት መቻሉን ዶክተር አበባየሁ ገልጸዋል።

የአገርን ብልፅግና እውን ለማድረግ ሁሉም ዜጋ የድርሻውን ለማበርከት መጣር እንዳለበት የገለፁት የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም ኣታ በተቋማት ደረጃ የአሰራር ችግሮችን ለመቅረፍ የሪፎርም ሥራዎች መጠናከሩ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ መቻሉንም አንስተዋል ።

የተጀመሩ አገራዊ ፕሮጀክቶችን በማስቀጠል የሚፈለገውን ግብ ለመድረስ ብርቱ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝም ተገልጿል ።

የቱሪዝም ዘርፉን በማሳደግ የአገሪቱን የገቢ አቅም ከፍ በማድረግ አበረታች ለዉጥ ማምጣት የሚቻልበትን አጋጣሚ መፈጠሩን አቶ አብርሃም አታ ገልጸዋል ።

የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ምሥረታ በዓልና ዞናዊ ማጠቃለያ መርሐግብር በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል ።

ዘጋቢ፡ ዳኜ ጥላሁን – ከጂንካ ጣቢያችን