ተገቢውን የሕክምና አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውን አንዳንድ የሀላባ ቁልቶ አጠቃላይ ሆስፒታል ተገልጋዮች ተናገሩ
የህክምና አገልግሎቱን ይበልጥ በማስፋትና በማሻሻል ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ ሆስፒታሉ አስታውቋል።
በሀላባ ቁልቶ አጠቃላይ ሆስፒታል አገልግሎት ለማግኘት በመጡበት ያነጋገርናቸው ተገልጋዮች፤ በሆስፒታሉ የሚሰጠው አገልግሎት እየተሻሻለ መምጣቱን ጠቁመው ከዚህ ቀደም ለህክምና ረጂም ርቀት በመጓዝ ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና ይዳረጉ እንደነበር አንስተዋል።
አስተያየት ሰጪዎቹ በሆስፒታሉ በፊት ያልነበሩ የህክምና አገልግሎቶችንም እያገኙ መሆናቸውን ጠቁመው ከመድኃኒት እጥረት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮች መቀረፍ እንዳለባቸው ጠይቀዋል።
ሆስፒታሉ የአገልግሎት ዘርፉን በማሻሻልና በማስፋት በስፔሻሊስቶች የታገዘ የጤና አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ከይረዲን ሀቢብ ገልፀዋል።
በሆስፒታሉ የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል ከሌሎች አጠቃላይ ሆስፒታሎች የተሻለ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
የሆስፒታሉን ቅጥር ግቢ ውብና ማራኪ ሆኖ ተገልጋዮች እርካታ እንዲያገኙ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነ ስራ አስኪያጁ ጠቁመዋል።
በሆስፒታሉ የማህጸን ጫፍ ካንሰር እና የደም ግፊት ቅድመ ምርመራና ህክምና አገልግሎት ያለምንም ክፍያ እየተሰጠ ስለመሆኑም ዶክተር ከይረዲን ገልጸዋል።
የመድኃኒት እጥረት ችግሮችን ለመቅረፍ በተደረገው ጥረት በዞኑ አስተዳደር እና በሆስፒታሉ ድጋፍ የማህበረሰብ መድኃኒት ቤት ተከፍቶ ተገልጋዮች መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያገኙበት ዕድል መፈጠሩንም ስራ አስኪያጁ አስረድተዋል።
በሆስፒታሉ የጤና መረጃ አያያዝን በማዘመን ከወረቀት የፀዳ አገልግሎት ለመስጠት የህክምና ግብዓቶችን ለማሟላት በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ ነው ብለዋል።
ዘጋቢ: አብዱልሰመድ አወል – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ሥራ ከዳር ለማድረስ በሚደረገው ርብርብ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሙዱላ ከተማ አስተዳደር ገለፀ
በትምህርት ሴክተር የመረጃ አያያዝ ውጤታማነት ዙሪያ በኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
ሁሉንም የመማሪያ መጻሕፍት ባለማግኘታቸው በትምህርታቸው ላይ ጫና እየፈጠረባቸው መሆኑን በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የቆንጋና ቆቄ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተናገሩ