የጂንካ ዩኒቨርሲቲ አዲስ አፈር አልባ የመኖ አመራረት ዘዴን አስተዋወቀ
(Hydrophoncs Green Fodder production technology) በመባል የሚታወቀውና ያለ አፈር በውሃ ብቻ የሚከናወን የመኖ አመራረት ስርዓት ሲሆን አውሮፓን ጨምሮ ሌሎች ሐገራትም የሚጠቀሙበት ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ነው።
የተለያዩ የሰብል አይነቶችን በቀላሉ ማምረት የሚያስችለው ይህ ቴክኖሎጂ በእንሰሳት ሀብት ልማት ዘርፍ በተለይም የእንሰሳት ተዋጽኦን ምርታማነት ከፍ በማድረግ ረገድ ያለው አስተዋጾ ከፍተኛ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።
በዩኒቨርሲቲው የተጀመረው አዲሱ የአፈር አልባ የመኖ አመራረት ስልትን በማህበረሰቡ ለማስፋፋት ይቻል ዘንድ የተደረገ የመስክ ምልከታም ተካሂዷል።
አፈር አልባ የመኖ አመራረት ስርዓቱም በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንትን ዶ/ር ኩሴ ጉድሼ፣ የአስተዳደር ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር አለሙ አይለቴን ጨምሮ ሌሎች ባላድርሻ አካላትም ተጎብኝቷል።
ዘጋቢ ፡ አርሻል አራቦ – ከጂንካ ቅርንጫፍ ጣቢያ
More Stories
አሰልጣኞች ወቅቱ የሚጠይቀውን የቴክኖሎጂ ክህሎት እንዲላበሱ እየተሠራ መሆኑ ተጠቆመ
በቴክኖሎጂ የተካኑ ዜጎችን ለማፍራት በትኩረት በመሥራት ሀገሪቱን ማበልጸግ እንደሚገባ ተገለጸ
በቴክኖሎጂና ፈጠራ ተወዳዳሪ የሰው ኃይል በማፍራት የኢንዱስትሪ ሽግግርን በማፋጠን የሃገር ኢኮኖሚ እንዲያድግ እየሰራ መሆኑን በስልጤ ዞን የቂልጦ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ገለፀ