በኮሬ ዞን የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት እየተሰጠ ነው – የዞኑ ጤና ዩኒት

በኮሬ ዞን የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት እየተሰጠ ነው – የዞኑ ጤና ዩኒት

በዞኑ ከ 9 እስከ 14 ዕድሜ  ለሆናቸው ከ27 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሴቶች የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት እንደሚሰጥም ተገልጿል።

የኮሬ ዞን ጤና ዩኒት ኃላፊ አቶ ደመላሽ ሺፈራው እንደገለጹት ክትባቱ መሰጠት ከመጀመሩ በፊት ለማህበረሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራዎችን ከጤና ባለሙያዎች፣ ከሐይማኖት ተቋማት ፣ ከባለድርሻዎች እና ከሚዲያ አካላት ጋር  ሲሰራ ቆይቷል።

የማህጸን በር ካንሰር በዋናነት ሂውማን ፓፒሎማ በተሰኝ ቫይረስ አማካይነት  የሚከሰት ሲሆን በሽታውን ለመከላከል  የመጀመሪያው የመከላከያ ክትባቱን መውሰድ እንደሆነ የገለጹት አቶ ደምበላሽ በተለይ ዕድሜያቸው ከ 9 እስከ 14 ዓመት የሆናቸው ሴት ልጆች መከተብ አለባቸው ብለዋል ።

ሲሰተር ባዪሽ ዊጋ በኮሬ ዞን የከሌ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ሲሆኑ፣  ክትባቱ  የሴቶችን ተጋላጭነት ለመቀነስ አስፈላጊ እንደሆነ አንስተው ማህበረሰቡ ሴት ልጆቻቸውን በማስከተብ የሚጠበቅባቸውን ሚና መጫወት እንዳለባቸው ገልፀዋል ።

 በሐገር አቀፍ ደረጃ ከህዳር 9 ጀምሮ የሚሰጠውን የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት  በኮሬ ዞን በሁለቱም ወረዳዎችና በከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ክትባቱ በመሰጠት ላይ ይገኛል ።

ዛጋቢ ፡ ለምለም ኦርሳ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን