የሀገር መሠረትና ተስፋ በሆኑ ህጻናትና ሴቶች የሚደርሰው መጠነ ሰፊ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጥቃት በሚያስከትለው ጉዳት ልክ ተመጣጣኝና አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ የጌዴኦ ዞን ህጻናት ፓርላማ ገልጿል፡፡
ዓለም አቀፍ የህፃናት ቀን በዓለም ለ35ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደረጃ ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ “ህጻናት የሚሉት አላቸው እናድምጣቸው” በሚል መሪ ቃል እንዲሁም የዓለም የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀን በዓለም ለ33ኛ ጊዜ በሀገራችን ደረጃ ለ19 ኛ ጊዜ “የሴቷ ጥቃት የእኔም ነው፤ ዝም አልልም” በሚል መሪ ቃል በዞኑ ዲላ ከተማ ተከብሯል፡፡
የጌዴኦ ዞን ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ፍሬነሽ አየለ በዕለቱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ባስከተለው ዕልቂት ሳቢያ ያለአሳዳጊ የቀሩትን ህፃናት መብት ለማስከበር በማሰብ መከበር የጀመረው የዓለም የህፃናት ቀን ከመረሀ ግብሩ ባለፈ በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጥቃቶችን ከመመከት አኳያ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በዞን ደረጃም የህጻናት እና ሴቶችን አካላዊም ሆነ ሥነ ልቦናዊ ጥቃቶችን ለመከላከል በተሰሩ ሥራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መመዝገባቸውን የጠቆሙት ወይዘሮ ፍሬነሽ፤ ሴቶችና ህጻናት በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ያላቸውን ሚና እንዲወጡ ቀርበን ልናዳምጣቸው እና ልንደግፋቸው ይገባል ብለዋል፡፡
የጌዴኦ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ ታጠቅ ዶሪ (ዕጩ ዶክተር) የተሻለች የነገዋን ኢትዮጵያ ለማየት ያለን ተስፋ ዕውን የሚሆነው ዛሬ በህፃናት ላይ በምንጥለው መሠረት መሆኑን በመገንዘብ፤ ለህጻናት ተገቢውን እንክብካቤና ፍቅር ልንሰጣቸው ይገባል ብለዋል፡፡
የአሁኑ ትውልድ ከነገሮች ጋር በፍጥነት የመላመድ ችሎታ ያላቸው በመሆኑ ዕድገታቸውንና የነገ ተስፋቸውን ከሚያጨልሙ መጤ ባህሎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ከማገዝ አኳያ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባም ምክትል አስተዳዳሪው አሳስበዋል፡፡
የጌዴኦ ዞን ህፃናት ፓርላማ ዋና አፈ ጉባኤ ዱሬቲ አሸናፊ፤ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በህፃናት ላይ እየተፈፀሙ ያሉ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጥቃቶች መጠነ ሰፊ ቢሆኑም ከሚያስከትሉት ጉዳት አኳያ ተመጣጣኝና አስተማሪ እርምጃ ከመውሰድ ረገድ ያሉ ውስንነቶች በቀጣይ ሊቀረፉ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ: ሳሙኤል በቀለ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
“ዞናዊ አንድነት ለጋራ ህልሞቻችን ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የዞኑ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላትን ጨምሮ የዞኑ ተወላጅ የክልል አመራሮች የዞን ጠቅላላ አመራር እና የየወረዳ የፊት አመራሮች የምክክር መድረክ በደቡብ ኦሞ ዞን ዲመካ ከተማ እየተካሄደ ነዉ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት የበጀት ቀመር አሰራርና የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ይገኛል
በዳውሮ ዞን ማረቃ ወረዳ የዋካ ከተማ በአዲሱ መዋቅር የከተማ አስተዳደር በማግኘቷ መደሰታቸውን ነዋሪዎቿ ገለፁ