ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ በመመዝገብ የሚፈልገውን የፖለቲካ ፓርቲ እንዲመርጥ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ጥሪ አቀረበ
ፓርቲው በምርጫ ስነ-ምግባር ዙሪያ ከእጩዎቹ እና አመራሩ ጋር ውይይት በሚዛን አማን ከተማ አካሂዷል።
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን አማን ከተማ ከእጩዎቹ እና ከአመራሩ ጋር ባደረገው የምርጫ ስነ-ምግባር ውይይት ላይ የቤንች ሸኮ እና የሸካ ዞን ኢዜማ አስተባባሪው አቶ ተፈራ በዛብህ እንደተናገሩት፤ በሁለቱ ዞኖች ለተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤት አባላት ምርጫ እጩዎቻቸውን ለምርጫው ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል።
ለምርጫው ሂደትም ህብረተሰቡ ከወዲሁ በመውጣት በመመዝገብ ካርድ መያዝ ይገባቸዋልም ብለዋል።
ምርጫው ነጻ፣ ፍትሀዊ ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ከአባሎቻቸው ጋር በምርጫ ስነ-ምግባር ውይይት ማድረጋቸውንም ነው የተናገሩት።
ሰላም ከምንም በላይ አስፈላጊ ነው ያሉት አቶ ተፈራ፤ ሰላማዊ ምርጫ እንዲካሄድ እና ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ ፓርቲያቸው እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
የሚዛን ምርጫ ክልል ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋር ምክር ቤት ሰብሳቢ እና የኢዜማ ሰብሳቢ አቶ ብርሀኑ ገብረመድህን በበኩላቸው፤ በሚዛን ምርጫ ክልል ፓርቲያቸው ኢዜማ አንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና አስር የክልል ምክር ቤት አጩዎችን ለምርጫ ማዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።
ምርጫው ነጻ፣ ፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር እየሰሩ መሆኑን ጠቁመው ህዝቡም በነቂስ በመውጣት ተመዝግቦ ካርድ በመውሰድ የሚፈልገውን ፓርቲ በድምጹ ማረጋገጥ ይገባዋል ብለዋል።
ከአባሎቻቸው መካከል አቶ ጋሻው አዲሱ እና መምህርት ማስረሻ ጥላሁን እንዲሁም መምህርት ባንቺአየሁ በላይ እንደተናገሩት ምርጫው ነጻ፣ ፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ጠቁመዋል።
ህብረተሰቡም በምርጫ ምዝገባ ወቅት በመውጣት በመመዝገብ ድምጹን ለሚፈልገው ፓርቲ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
ሰላም በማስጠበቅ ረገድም የበኩላቸውን ድርሻ ለማበርከት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
ዘጋቢ: አብዮት በቀለ – ከሚዛን ጣቢያችን

More Stories
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች በዘላቂነት እንዲመለሱ ከየትኛውም ጊዜ በላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኧሌ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ገለፀ
መንግስት የደን ጭፍጨፋን በመከላከል የአየር ሚዛንን ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ እስታውቀ
የህዝቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ እንዲያስችል ዞኑ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ