በፍርድ ቤቶችና በፍትህ ዘርፉ የሚታዩ የአገልግሎት ጥራትና የስነ-ምግባር ችግሮችን ለመቅረፍ በቅንጅት መስራት ይገባቸዋል – ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ
ሀዋሳ፡ ሕዳር 04/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በፍርድ ቤቶችና በፍትህ ዘርፉ የሚታዩ የአገልግሎት ጥራትና የስነ-ምግባር ችግሮችን ለመቅረፍ በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ ገለፁ።
በክልሉ የፍትህ አሰጣጥን ለማሻሻል እየተደረገ ባለው የምክክር መድረክ ንግግር ያደረጉት አፈ ጉባኤዋ የፍትህ ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ውስን መሆን የህዝቦችን የፍትህ እርካታ እውን እንዳይሆን አድርጓል ብለዋል።
እንደ ሀገርም ዘርፉን ለማዘመን ባለፈው አንድ አመት ፍኖተ ካርታ ተቀርጾ እየተሰራ ቢሆንም የስነ-ምግባርና የገለልተኝነት ችግሮች አሁንም ስራ የሚጠይቁ ስለመሆናቸው አንስተዋል።
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሴኖ አቡሬ፤ የተፈጠረው መድረክ ፍርድ ቤቱ ገለልተኝነቱን በጠበቀ መልኩ ከፍትህ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ እንዲሰራ አስቻይ ነው ብለዋል።
በተለይም ህግና ስርዓትን በተፃረረ መልኩ የሚሰሩ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግና የጠራ አቋምን ይዞ ለመሄድ ቅንጅታዊ ስራዎች ይጠይቃሉ ብለዋል።
የፍትህ አሰጣጡን ለማዘመን የዲጂታል(በቴክኖሎጂ የታገዘ) የዳኝነት ስርዓት እየተዘረጋ ስለመሆኑም ተመላክቷል።
ዘጋቢ፡ ባዬ በልስቲ

 
                 
                                         
                                         
                                         
                                        
More Stories
የአፍላ ወጣቶችና ወጣቶችን የስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ለመቅረፍ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጎልበት የጤና አደረጃጀቶችን ሚና ማሳደግ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ
ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመግባት ዕድል ያገኙ ተማሪዎች የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ትምህርታቸው ላይ ብቻ ሊያተኩሩ እንደሚገባ መልዕክት ተላለፈ
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ከ10 ቢልዮን ብር በላይ በጀት ለተለያዩ የልማት ስራዎች እንዲውል በተገቢው እንደሚሠራ ገለፀ