በቶሮንቶ ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ አሸነፉ
በቶሮንቶ በተካሄደ የማራቶን ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ አሸንፈዋል።
በሴቶች ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከ1ኛ – 3ኛ በመግባት የበላይ ሆነው አጠናቀዋል።
በውድድሩ አትሌት ዋጋነሽ መካሻ 2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ44 ሴኮንድ 1ኛ ስትወጣ አትሌት ሮዛ ደረጀ 2ኛ እንዲሁም አትሌት አፈራ ጎድፋይ 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል።
በሌላ በኩል በወንዶች ማራቶን አትሌት ሙሉጌታ ኡማ 2 ሰዓት ከ07 ደቂቃ ከ16 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት ውድድሩን ማሸነፍ ችሏል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
በ5000 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ 3 ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለፍፃሜ ደረሱ
ስፔን ከ11 ዓመታት በኋላ የቀዳሚነቱን ቦታ ያዘች
አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኖ ወደ ቤኔፊካ