አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝ ሆኑ
የቀድሞው የአርባምንጭ ከተማ እና ወላይታ ድቻ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል።
በዚህም ላለፉት 12 ወራት የብሔራዊ ቡድኑ ምክትል አሰልጣኝ የነበሩት መሳይ ተፈሪ በቀጣይ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ(ቻን) ማጣሪያ ከኤርትራ ጋር የምታከናውናቸውን ጨዋታዎች ጨምሮ የቻን ማጣሪያን በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝ የሚመሩ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል።
ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር የምታደርጋቸው የደርሶ መልስ ጨዋታዎች በደቡብ ሱዳን ጁባ ብሔራዊ ስታዲየም የሚከናወኑ መሆኑን የፌዴሬሽኑ መረጃ አመላክቷል።
ጨዋታዎቹ የሚከናወኑበት ቀናትም ጥቅምት 21/2017 እና ጥቅምት 24/2017 ናቸው ተብሏል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ሊቨርፑል ለአሌክሳንደር አይዛክ በድጋሚ የዝውውር ጥያቄ ሊያቀርብ ነው
ሮድሪ እና ዳኒ ካርቭሃል ከ12 ወራት በኋላ ወደ ስፔን ብሔራዊ ቡድን ተመለሱ
አርሰናል የፒኤሮ ሂንካፔን ዝውውር ከማጠናቀቁ አስቀድሞ ሁለት ተከላካዮቹ ክለቡን ሊለቁ ነው