ማንቸስተር ሲቲ በባከነ ደቂቃ በተቆጠረ ግብ ዎልቭስን አሸነፈ
በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ 8ኛ ሳምንት መርሐግብር ከሜዳው ውጪ ዎልቭስን የገጠመው ማንቸስተር ሲቲ በተጨማሪ ሰዓት በተቆጠረ ግብ ዎልቭስን 2ለ1 አሸንፏል።
በሞሊኑክስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጆስኮ ግቫርዲዮል በ33ኛው ደቂቃ እና ጆን ስቶንስ በ90+5 የማንቸስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።
ስትራንድ ላርሰን በ7ኛ ደቂቃ የዎልቭስን ጎል አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ ማንቸስተር ሲቲ በ20 ነጥብ በጊዜያዊነት የሊጉ መሪ መሆን ሲችል ዎልቭስ በ1 ነጥብ 20ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ፕሪሚዬር ሊጉ መካሄዱን ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ላይ በአንፊልድ ሮድ ሊቨርፑል ከቼልሲ ተጠባቂ ጨዋታ የሚያከናውኑ ይሆናል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ሆዜ ሞሪንሆ እና ዲዬጎ ሲምዮኔ ከ12 ዓመታት በኋላ በማድሪድ ደርቢ ይፋለማሉ
የሪያል ማድሪድ ትኩረት በ ማንችስተር ዩናይትድ ታዳጊ ጄጄ ጋብርኤል ላይ
“ከማክስ ዶውማን ጋር መስራት ትልቅ ደስታ ነው” ሚኬል አርቴታ