የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ የለውጡ መንግስት ባለፉት ዓመታት ታላላቅ ሪፎርም ሥራዎችን ማከናወን መቻሉን ገልፀው በተለይም በሲቪል ሰርቪሱ ዘርፍ ተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ የፖሊስና ስትራቴጂ ለውጦችን በማከናወን በየደረጃው የተከናወነውን ለውጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተግባራዊ ለማድረግ መረባረብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በቀጣይም በሁሉም ዘርፍ የመጡ የሪፎርም ውጤቶችን በማስቀጠል አንድነቷ የተረጋገጠ ሀገር እንዲገነባ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዋኖ ዋሎሌ በንግግራቸው ባለፉት ዘመናት ብሔርተኝነትና ፅንፈኝነት የሰፈነበት ሥርዓት፣ የነጠላ ትርክት የበላይነት ወሰዶ በማሸማቀቅ ይመራ ከነበረበት የፖለቲካ ሥርዓት ወጥተን በውል ትርክት አሰተሳሰብና የመሐል የፖለቲካ ሪፎርም እንድንከተል ያስቻለ ነው ብለዋል።
አክለውም በቴክኖሎጂ ግብርናውን በማዘመን፣የሳይንስ ሙዝየምና ሌሎችም የሚጠቀሱ ሲሆን በተለይም የሲቪል ሰርቫንት ፖሊስ ሥርዓቱ ተዘርግቶ እንዲመራ ያስቻለ የብልፅግና ትሩፋት ውጤት መሆኑን አንስተዋል።
በዕለቱም በትምህርት፣ በኢኮኖሚ ዘርፍ፣ በቴክኖሎጂ ዘርፍ በሲቪል ሰርቪስና በፍትህ ዘርፍ የነበሩ ሪፎሪሞችን የሚዳስስ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡
የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ አመራሮችና ባለሙያዎች የዕውቅና ሽልማት በመሰጠት መድረኩ ተጠናቋል።
ዘጋቢ: ከተማ በየነ ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል እንደፈጠሩ የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ
የኣሪ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ የሴቶች ሚናን በተመለከተ የጋራ ውይይት በጂንካ ከተማ ተካሄደ
ህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ ሁሉም በትጋት ሊሰራ እንደሚገባ የጌዴኦ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ገለጸ