“ሃይማኖቶች ለሰላም፣ ለመከባበር እና ለአንድነት” በሚል መሪ ቃል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሃይማኖት ተቋማት ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ብፁዕ አቡነ ህርያቆስ የአዲስ አበባና ሀዲያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ፓትርያርኩና የኢሃተጉ የበላይ ጠባቂ ተወካይ፣ ክቡር ሽይኽ አብዱልከሪም ሽይኽ በድረዲን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንትና የኢሃተጉ የበላይ ጠባቂ ተወካይ፣ ክቡር ቄስ ደረጀ ጀምበሩ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዝዳንትና የኢሃተጉ የበላይ ጠባቂ ተወካይ፣ ብፁዕ አቡነ ስዩም ፍራንሷ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የብፁዕ ካርዲናልና የኢሃተጉ የበላይ ጠባቂ ተወካይ፣ ፓስተር ታደሠ አዱኛ የኢትዮጵያ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ፕሬዝዳንትና የኢሃተጉ የበላይ ጠባቂ ተወካይ እንዲሁም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር እና የዕለቱ የክብር እንግዳ እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) ጨምሮ የሃይማኖት መሪዎች የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ሀድያ ዞን እና የሆሣዕና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የሁሉም ቤተ-እምነት ተከታዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በአሁኑ ሰዓት በየሃይማኖቱ ወጣት መዘምራን መንፈሳዊ መዝሙሮች እየቀረቡ ይገኛል፡፡
ዘጋቢ፡ በየነ ሰላሙ – ከሆሳዕና ጣቢያችን

More Stories
ህዝበ ክርስቲያኑ የ2019 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ በዓልን በሚያከብርበት ወቅት አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሀይማኖት አባቶች ተናገሩ
የ2018 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የዲጂታል ሽግግር የሉዓላዊነቷ ምሰሶ መሆን የቻለችበት አመት መሆኑን አቶ አልማው ዘውዴ ገለፁ
ጳጕሜን 5 “የነገው ቀን” በኮሬ ዞን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው