አስገራሚው የምርጫ ውጤት

በፈረኦን ደበበ

የየሀገራትን ተጨባጭ ሁኔታ ሳንገነዘብ ትንታኔ መስጠቱ ትክክለኛ አይደለም፡፡ ነገር ግን አንዳንድ የምርጫ ውጤቶች ላይ በማይመስል መልክ ውጤት መመዝገቡ አስገራሚ ሆኗል፡፡ የብዙ ምርጫ ጣቢያ ውጤቶች ገና ይፋ ባልሆኑበት ሁኔታ ሰሞኑን በተካሄደው የሩዋንዳ ጠቅላላ ምርጫ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ 99 በመቶ አሽንፈዋል መባሉ የብዙዎችን ጆሮና ልብ ከህዝብ ጋር እጅና ጓንት ሆነው ስለሠሩ ነው የሚለውንም ሀሳብ እንድንመዝን ይገፋፋናል፡፡

ምክንያቱም ፕሬዝዳንቱ ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎችም ያልተናነሰ ስቧል፡፡ እንዲህም አለ እንዴ¡ ብለው እንዲያስቡም አድርጓቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በተቃዋሚዎች ላይ “ጫና አድርገዋል” የሚለውን የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ወቀሳ እንኳን ወዲያ ብለን ከህዝብ ጋር እጅና ጓንት ሆነው ስለሠሩ ነው የሚለውንም ሀሳብ እንድንመዝን ይገፋፋናል፡፡ ምክንያቱም ፕሬዝዳንቱ ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎችም ያልተናነሰ ውጤት አስመዝግበው ስለሚያውቁ፡፡ ከዚህ አንጻር ያሁኑ ውጤት የዓመቱ የዓለም ክብረ-ወሰን ተደርጎም ይወሰዳል ፓርቲዎች አንገት ለአንገት ተናንቀው በተወዳደሩባቸው ሀገራት የደረሰባቸውን ከተመለከትን፡፡

ዘንድሮ በአፍሪካ አህጉር በተለይም በደቡብ አፍሪካ የተመዘገበው ውጤት የዚህ ግልጽ ማሳያ ነው በርዕዮተ ዓለምና በዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ልዩ የሆኑትን የአውሮፓና ሌሎች ሀገራትን እንኳን ባንቆጥር፡፡ ጠይም፣ ቀጭንና ረጅም ቁመና ያላቸው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ እስካሁን ሩብ ምዕተ-ዓመት ለሚሆን ጊዜ ሀገሪቱን በመምራት በአህጉሪቱ አንቱ ከተባሉ መሪዎች አንዱ ሲሆኑ ያሳለፏቸው ሦስት የምርጫ አመታት አልበቃቸውም ወይ የሚል ጠያቂዎችንም ፈጥረዋል ሰሞኑን ለአራተኛ ዙር የገቡበትን ውድድር ማሰቡ ይቅርና፡፡

ውጤቱ አብዛኞች ተቃዋሚ አካላት ከጠበቁት ለየት ማለቱ አስገራሚ ሆኗል አርጅቻለሁ በቃኝ ብለው ይተዋሉ ተብሎ በተጠበቁበት በማስመዝገባቸው፡፡ እሳቸው 99 ወይም 100 በመቶ ማለቱን የፈሩ ይመስል “ከቁጥርም በላይ ነው” ማለታቸው ምሥጢሩን ለመግለጽ ረድቷቸዋል፡፡ የውጤቱን አስገራሚነት የሚገልጹ በርካታ ማሳያዎች ያሉና ይህም በተለይ ከምዕራባዊያን ሀገራት ጋር ሆድና ጀርባ ቢያደርጋቸውም በመሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ ከታሪክ፣ ከህብረተሰቡ ዕድገት ደረጃ እና መሪው ከህዝብ ጋር ያላቸውን መስተጋብር ሁሉ እንድናነሳ ያስገድደናል፣ ተግባራዊ እያደረጓቸው ያሉትን የልማት ፖሊሲዎችን እንኳን ባንቆጥር፡፡

ታዳጊ ሀገራትና እንዲሁም የአፍሪካ ሀገራት ተግባራዊ እያደረጋቸው ያላቸው የልማት ፖሊሲዎችን ከወሰድን ሀገሪቱ ግንባር ቀደም ተብላ ትጠቀሳለች፡፡ ፕሬዝዳንቱ ላለፉት በርካታ ዓመታት የህዝቡ መሠረታዊ በሆኑ ፍላጎቶች ማለትም በመሠረተ ልማት ማስፋፊያዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ድህነትን መቀነስ እንደቻሉ ነው የመገናኛ ብዙሀንና አስተያየት ሰጪ ዜጎች የሚያስረዱት፡፡ ክብረ-ወሰን በእርግጥ ዓለም በኑሮ ውድነት፣ በድርቅና በኃይል እጥረት ችግሮች እየተናጠች ባለችበት ወቅት ተመዘገበ የተባለው ከ7 ነጥብ በላይ የምጣኔ ሀብት ዕድገትም ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ ሀገሪቱን ከሌሎች ሀገራት ልዩ የሚያደርጋትን የሠላምና ጸጥታ ጉዳይ ከወሰድንም ለአብነት የሚጠቀስ ነው ምክንያቱም ከዓመታት በፊት አስከፊ የሆነ የዘር ማጥፋት ችግር አልፋ ስለመጣች። ከ14 ሚሊዮን በላይ ህዝብ እንዳላት በሚነገርላት ሀገር አሁን በመተሳሰብ ላይ የተመሠረተው ማህበራዊ መስተጋብር ሁሉ የመንግሥት ገንቢ ሚና ውጤት እንደሆነ ነው የሚነገረው፡፡

የሩዋንዳ አርበኞች ግንባር የተባለውን ገዢ ፓርቲ እየመሩ እስካሁን ያደረሱት የ66 ዓመቱ ካጋሜ ከሰሞንኛ ውጤት በኋላ ያስተላለፉት መልዕክትም ውጤቱ ከህዝብ ጋር ያለውን የጠበቀ ቁርኝት የሚያሳብቅ ነው፡፡ የተገኘው ውጤት ከፍተኛ እንደሆነና “ይህ ቁጥር ብቻ አይደለም” በማለትም ገልጸዋል ዋናው ነገር ተአማኒነት መሆኑን ለማመልከት፡፡ ብዙ ጠንካራ ጎኖች የሚነገሩላቸው ፕሬዝዳንት ግን ሊያሻሽሉ የሚገባቸው በርካታ ችግሮች እንዳሉባቸውም ነው በሌላ በኩል የሚገለጸው፡፡ ከሰብአዊ መብት ረገጣ እስከ ሥልጣናቸውን ማራዘሚያ ህገ-መንግሥት ማሻሻያ ድረስ የወሰዷቸው እርምጃዎች ሁሉ ለተለያዩ ወቀሳዎችም ዳርጓቸዋል፡፡

በተለይ ኒው ዮርክ ታይምስ የተባለው ጋዜጣ እና ሌሎች መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት ከሆነ በተቃዋሚዎች ላይ የሚፈጸመው እንግልትና ሰቆቃ ከፍተኛ ነው ብዙዎችን ለፍርሀትና ሥጋት ስለዳረጋቸው፡፡ ዋና ተቃዋሚ ፓርቲን ጨምሮ አብዛኞች ተቀናቃኞች በእሥር ቤት መሆናቸውም በሥርዓታቸው ላይ ጥያቄ ያስነሳል ምክንያቱም ካጋሜ የተወዳደሩት “ከራሳቸው ጋር እንጂ ከማንም ጋር” ያለመሆኑ ይፋ ስለሚወጣ፡፡ አቋማቸው ባለፈው በሴኔጋል ከተደረገው ማሻሻያም ይለያል ምክንያቱም ከእሥር ቤት የወጡ ተቃዋሚዎች የምርጫ አሽናፊ ሆነው ብቅ ስላሉ፡፡ ከአሁኑ ምርጫ ጋር አገናኝተን ስንመለከት ወደ ምርጫው የገቡ ሁለቱ ፓርቲዎችም ቢሆኑ አቅም የሌላቸው መሆናቸው የታሰበውን ያህል ምቾት የሚሰጣቸው አልሆነም፡፡ የደቡብ አፍሪካና በአህጉሪቱ ያሉ ሌሎች ስመ-ጥር ገዢ ፓርቲዎች ተሞክሮም እንደሚያሳየው ዴሞክራሲ ካልተገነባ በቀር በልማት ብቻ ህዝብን እያማለሉ መቆየት የትም አያደርስም፡፡

በአሁኑ ጊዜ ትንሽ የምትመስለው ችግር ወደፊት የተለያዩ ውጫዊ አካላት ሁሉ ሲቀላቀሉበት አድማሱን እያሰፋ ሀገር እስከ መጉዳት ሊደርስም ይችላል፡፡ ስለሆነም መንግሥት በያዘው ጠንካራ ጎኑ ላይ ክፍተቶቹን ፈትሾ ጠንካራ ሀገር መገንባትም ይጠበቅበታል ፕሬዝዳንቱ ሲናገሩ “በአብሮነት ሁሉንም ችግሮች እፈታለን” ያሉትን ለመተግበር፡፡