አርባምንጭ ከተማ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚዬርሊግ መመለሱን አረጋገጠ
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ተሳታፊ የሆነው አርባምንጭ ከተማ ቀሪ 3 ጨዋታዎች እያሉት ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚዬርሊግ ማደጉን አረጋግጧል።
አርባምንጭ ከተማ ወደ ፕሪሚዬር ሊጉ ማደጉን ያረጋገጠው በዛሬው ዕለት በ23ኛ ሳምንት ቦዲቲ ከተማን 2 ለ 0 አሸንፎ ነው።
ክለቡ በ2015 የውድድር ዘመን ከፕሪሚዬርሊጉ ወደ ከፍተኛ ሊጉ የወረደ ሲሆን በወረደበት ዓመት ወደ ሃገሪቱ ቀዳሚው የሊግ እርከን መመለስ ችሏል
አዘጋጅ ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ካርሎስ ባሌባ ለማንቼስተር ዩናይትድ ፊርማውን አኖረ
አርሰናል ከ ላምፓርዱ ኮቨንተሪ ሲቲ
አርሰናል ኤዝሪ ኮንሳን በ55 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ አስፈረመ